Get Mystery Box with random crypto!

Y Ethio class

Logotipo del canal de telegramas questions_for_all - Y Ethio class Y
Logotipo del canal de telegramas questions_for_all - Y Ethio class
DirecciĂłn del canal: @questions_for_all
CategorĂ­as: Sin categorĂ­a
Idioma: EspaĂąol
Suscriptores: 734
DescripciĂłn del canal

ማንኛውንም ጠቃሚ እና ትምህርታዊ እንዲሁም የጠቅላላ እውቀት ጥያቄዎችን የያዘ chanal ነው።
please
#share
#share

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


Los Ăşltimos mensajes

2022-08-02 02:27:46 https://youtube.com/shorts/_RBrFl2h8Io?feature=share

ይህ ንግግር "ትምህርት ብቻ" ለምትሉ ሰዎች አሪፍ መልእክት ነው
136 viewsedited  23:27
Abrir / CĂłmo
2022-07-29 08:56:18 ​​የምትገኝ ፈለክ ስለሆነች ነው፡፡
ሌላው እንደመሬት ከአለት የተሰራች ፕላኔት ስለሆነች ይመስለኛል፡፡እውነታው
ማርስ ከመሬት በላይ በቀዝቃዛ አየር የታጠረች ነች..ግን እኔ እንዳየዋት
አይቼም እንደታዘብኮት ከመሬት ጋር ብዙ የሚያመሳስሎት ነገሮች አሉባት፡፡
አንደኛ ልክ እንደመሬት ወቅቶች ይፈራረቁባታል..ልክ እንደመሬት ተራራ እና
ሸለቆ አቀበትና ቁልቁለት ያላበት ነች…እንደውም ከኤበረስት በእጥፍ
የሚያስከነዳ ግዝፈት ያለው ተራራም ባለቤት ነች..ያንን በአይኔ ነው ያየውት
…ግን በገጽ ላይ ውሃ አይገኝባትም ወይም እኔ ማርስን በጎበኘውበት አጋጣሚ
ሁሉ የውሀ ጠብታውን እንኳን አጋጥሞኝ አያውቅም…፡፡
ስለዚህ ምድር የእግዚያብሄር ፀጋ ሚፈስባት ስፍራ ነች ያልኩት ዝም ብዬ
አይደለም፡፡እንደውም ሰው በምድር ቢያምን የምድር ጌታ ቢል ስህተት ሆኖ
ሊታሰብበት አይገባም ባይ ነኝ..ምክንያቱም የእጆቹ ስራ እጽብ ድንቅ በሆነ
ተዓምር የተገለጽው በምድር ላይ ነው…ሕይወት የሚፈጠረውም
የሚታደሰውም በምድር ላይ ነው……ምድር ራሷን እያደሰች የምትኖር ልዩ
ፈለክ ነች…
አረንጓዴ ደኖች ለምድር ፋሽናዊ ልብሶቾ ናቸው… በበጎነት እና በክፋት .ጥበብ
የተሞላው የሰው ልጅም ሹፌሯ ነው…በሰማይ የሚከንፍ አእዋፍቶች የምድር
ዋሽንቶቾ ናቸው…እንስሳቶቹ እና አራዊቶቾ የምድር ጌቶቾ ናቸው….ወንዝና
..ጅረቶቾ ….ሀይቆቾ እና ባህሮቾ ልቧን የሚያረሰርሱላት የእርጠበት መንፈሶች
ናቸው….
ሌላው ልነግራችሁ የምፍለገው ስለፀሀይ ነው፡፡ፀሀይ የተፈጥሮ ዋነኛዋ
ምስጥር ነች..ፀሐይ ሀይል ነች..ፀሐይ ህይወት ነች…ከእግዚያህብር የእጅ
ስራዎች ውስጥ ዋናዋ አስኮል ፀሀይ ነች…በግዝፈቷ ልክ አምቃ ያዘችውን
ኃይል አጃኢብ የሚያሰኝ ነው፡፡እራሷም የመለኮት እሳት ነች ቢባል ስህተት
አይሆንም፡፡
ለዛውም የሕይወት እሳት…እሷ መጥና የምትረጨው ብርሀን ነው ምድርን
በውበት እና በህይወት እንድትሞላ ያገዛት….አምላክ የፀሐይ አዛዥ ነው…
ሲያዛትም ለምድር ያደላ ይመስላል…አዳምን ፈጥሮ ወደምድር በስደት ነው
የላከው..ያ ማለት አባት ልጅን ሲቀጣ ሂድ መኝታ ቤትህ ግባ ብሎ ከሳሎን
እንደሚያባርረው አይነት ቅጣት ማለት ነው…፡፡ሳሎን ደስታ አለ ….ቴሌቬዝን
ማየት አለ…ፊልም መመልከት አለ….ወሬና ጫወታ አለ..፡፡መኝታ ቤት ግን
ትካዜ ነው..እንቅልፍና መደበት ነው፡፡በቃ ከዛ በላይ ግን ህመም የለውም…
ስቃይም አይገኝበትም…እግዚያብሄር አዳምን ወደ ምድር የላከውም ልክ
እንደዛ ባለ ስሌት ነው..እንጂማ ወደማርስ ሊልከው ይችል ነበር እኮ ..ወደ
ሜሪኩሪም..ወይ ወደ ጨረቃ…
…ግን የፀሀይ የስስት ውሽማ ወደሆነችውና በፍቅር ብርሀን እና በስስት
ሙቀት ወደምትጎበኘው ምድር ተላከ…በህይወት እና በተፈጥሮ በታጠረችው
ምድር ላይ መሪ ሆኖ ተሾመ …
….ጨረቃም ለምን ይቅርብኝ ብላ ከፀሀይ የለመነችውን ብርሀን ያለስስት
በምሽት ለምድር ትረጭላታለች…ይህ የእግዜያብሄር እጆች በምደር ላይ
ስለሆነ የሆነ ነገር ነው…ስለዚህ እያንዳንዶ የምድር ጥጋት በእግዜር ትንፋሽ
እና ፀጋ የተሸፈነ ነው…
….ለዛ ነው ምድር የእግዚያብሄር የፀጋው ማደሪያው ስለሆነች የቆምክባት
ምድር የተቀደሰች ነችና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ የተባለው…ስለአንድ
ክልል ስፍራ የተነገረ አይደለም…ጫማ ቆሻሻ መርገጫ ነው..ጫማ በሀጥያት
የተጨማለቀ የሰው ልጅ የክፍት ልብ ነው..በምድር ስትኖር የክፍት ልብ ካለህ
አውልቀህ ጣል ማለቱ ነው…
….ምድርን በፍቅር በምስጋና እና የምንኖርባት የእግዚያብሄር የእጆቹ ሰራ
መገለጫ ቅዱስ መቅደስ ነችና በወንጀል ልናቆሽሻት አይገባም …በጣርነት
ልናወድማት አይገባም….በመናጠቅ በሚመጣ ረሀብ የሰቆቃ እስር ቤት
ማድረግም አስፀያፊ ነው…፡፡
ይህ ሁሉ እንድንሾፍራት ለሰው ልጅ የተሰጠንን ሃላፊነት አላግባብ
በመጠቀም..የተወለወለው በፍቅር የተሞላው የአስፓልት መንገድ እያለ
በኮረኮንች እያንገጫገጩ ነድቶ ገደል መክተት ማለት ነው….ለምድር
ውድመት ዋናዎቹ ተጠያቂዎቹ እኛ ሹፌሮቹ የሰው ልጆች ነን..
በዚህ ህይወትና ብርሀኗን ስትለግሰን የኖረችው ፀሀይ ታዝንብናለች
እያዘነችብንም ነው..ለዚህ ነው ፀባዬ የሚቀያየረው …ስትበሳጭ እና
ስትነጫነጭ ነው፡፡ ከአቅም በላይ የሆነ ሙቀት እና ከአቅም በላይ
የሚሆንብንን ውርጭ የምትለቅብን…ጨረቃም አዝና ደም ስትለብስ
ምንታዘበው…እግዜር ትዕግስቱ ሆኖ ነው እንጂ እንደፀሀይ መቀየም የጀመረ
ቀን ፀሀይን መገሰፅ ያቆመ ቀን… ተስፋ የቆረጠብን ቀን በቃ..ምጽአት ያኔ
ነው…እናም እንደዛም የሚሆነው በገዛ ጥፋታችን ነው ባይ ነኝ፡፡
እኔ እና ንስሬ ዘጠና ፐርሰንት የሚሆነውን ጊዜያችንን የምናሳልፈው በዚሁ
በምድር ላይ ከምድርም በኢትዬጵያ ነው፡፡ይሄም የሆነበት ትውልድ ሀገሬ
ስለሆነች ብቻ አይደለም የራሱ የሆነ ሌላ ምክንያት አለው…. ያንን ወደፊት
ነው የምነግራችሁ፡፡ለአሁኑ ግን ላሳስባችሁ የምፈልገው ከአሁን ቡኃላ ከእኔ
የምትሰሙት ታሪክ በጣም አልፎ አልፎ ካልሆነ በስተቀር ሰለኢትዬጵያ ነው፡፡
ስለሀገሪቱ፤ስለታሪኮ፤ስለዜጎቾ፤ከንስሬ ጋር ስንለመረመርነው እና ስለታዘብነው
ሚስጥር…

ይቀጥላል....


Soryy ስለቆየዉ
10 comment ብቻ
138 viewsedited  05:56
Abrir / CĂłmo
2022-07-29 08:55:43 የዳቢሎሷ ልጅ

ምእራፍ

.
...
አሁን ወደራሴ ልመልሳችሁ፡፡ምክንያቱም እናቴ የጀመረችውን ታሪክ
ለመጨረስ እንዲህ በቀላሉ የምትችል አይነት አልመሰለኝም፡፡ይታያችሁ
እስከአሁን የአባቴን ከንፈር እንደሳመችው ወይም እንደሳማት እንኳን
አልገለፀችላችሁም፡፡እንግዲህ በዚህ አካሄዶ የእኔ መወለድ ጋር ለመድረስ
ስንት ምዕራፎችን መጠበቅ እንዳለባችሁ መገመት አይሳናችሁም ብዬ
አስባለው…እኔ ደግሞ ያን ያህል መጠበቅ አልችልም፡፡ባይሆን በመሀል
እለቅላትና የጀመረችውን ታሪክ ትጭስላላችሆለች፡፡
ለዛሬ ግን ራሴ ላውራችሁ..ስለዛሬ ..አሁን ስላለውበት ሁኔታ…
አሁን ያለውት አዲስ አበባ ነው ሲ ኤም ሲ አካባቢ ነው፡፡በነገራችን ላይ አዲስ
አበባ ብቅ ስል ማርፍበት የራሴ የሆነ ቤት አለኝ፡፡ 1ሺ ካ.ሬ ሜትር ግቢ ላይ
ጥጉን ይዞ በታነፀ ባለሶስት ክፍል መጠነኛ ቢላ ቤት ውስጥ ነው የምኖረው፡፡
….ከቤቱ ይልቅ በግቢ ውስጥ ያሉ ዛፎች ዕጻዋቶች እና ፍራፍሬዎች ይበልጥ
ያስደምማሉ፡፡ በግቢዬ ውስጥ ከ140 በላይ የዕፅዋት አይነቶች ይገኛሉ፡፡
ከነዚህ ውስጥ 83ቱን ከተለያዩ አህጉራት በዞርኩበት ወቅት ቀልቤን ስበውት
አወይም አስደምመውኝ አምጥቼ የተከልኮቸው ናቸው፡፡እርግጥ
አልዋሻችሁም አምጥቼ የተከልኮቸው ከዚህ አሁን ከጠቀስኩላችሁ ቁጥር
በሶስት እጥፍ ከፍ ያለ ነበር..ከአዲስ አበባ የአየር ፀባይ ጋር ተላምደው ግን
መጽደቅ የቻሉት እነዚህ ብቻ ናቸው፡፡
ግቢዬ ውስጥ ያሉ ዕጽዋቶች ሁሉ አስደማሚነታቸው ለአይን መስብ
ከመሆናቸውእና ንጽ አየር ሚያመርቱ ፋብሪካዎች ስለሆኑ ብቻ አይደለም
እዚህ ግቢ የመተከል ተተክሎም የመብቀል እድል ያገኙት…እያንዳንዱ የተለየ
ሚስጥር እና ጥበብ የሚገለጽባቸው የእግዚያብሄርን ሚስጥራዊ ሹክሹክታ
በቅጠሎቻቸው እና በስሮቻቸው ስለሚተነፍሱ ነው…::መድሀኑት ናቸው…
ታአምራትን የሚሰራባቸው ናቸው..ብዙ ብዙ ነገር…በየዛፎች ቅርንጫፍች ላይ
ቁጥራቸውን የማላውቃቸው የወፍ ጎጆዎች ሞልተውባቸዋል፡፡ሶስት ጉሬዛ እና
አራት ዝንጀሮዎችም አሉኝ ..ሁሉንም ያመጣዋቸው ከአገሬ ጫካ ነው… ከደሎ
መና፡፡
አብረውኝ የሚኖሩ አንድ የስልሳ ሁለት አመት አዛውንት ሰውዬ አሉ፡፡ጋሽ
ተክለወልድ ይማም ይባላሉ፡፡ይሄንን ጊቢ እንዲህ ያሳመርኩትም
የማስተዳድረውም ከእሳቸው ጋር ነው፡፡
እኔ ያው አብዝቼ ከአንድ የምድር ጫፍ ወደሌላው መስፈንጠር የዘወትር
ድርጊቴ ስለሆነ በሌለውበት ጊዜ እሳቸው ናቸው ሙሉ ሀላፊነቱን
የሚወስዱልኝ፡፡ዘበኛ ናቸው ወይም አትክልተኛ ናቸው እያልኩ አይደለም፡፡
ከዕጽዋቶች ጋር በፍቅር የወደቁ ከሀለማያ ዩኒቨርሲቲ ለ32 ዓመት ያስተማሩና
በቅርቡ ጡረታ የወጡ የዕጽዋት ተመራማሪ ፕሮፌሰር ናቸው፡፡ስለእሳቸው
ጠለቅ ያለ መረጃ ሌላ ጌዜ ነግራችሆለው ፡፡
በነገራችን ላይ ዋናውን ያለኝን ነገር አልነገርኮችሁም፡፡ንስር አሞራ አለኝ ፡፡
ንስር አሞራ ስላችሁ ሌላ ስለእሱ ለእናንተ የማስረዳበት መንገድ ስለሌለ ነው፡፡
እያንዳንዱ ሰው ልጅ እንዲጠብቀው እንዲንከባከበው እና ከክፉ ነገር
እንዲከልለው ከፈጣሪው የተመደበለት ጠባቂ መልዐክ አለው ብዬ
አምናለው፡፡ግን እነዚህ ጠባቂ መላዕክቶች አካል አልባ መንፈስ ናቸው ፡፡
አይታዩም፡፡መታየት ብቻ ሳይሆን አብዛኛው ሰውም ጠባቂ መልአኩን በትከሻው
ላይ ተሸክሞ እንደሚዞር አያውቅም… አያምንምም፡፡
ስለዚህ አይገለገልባቸውም …አያዳምጣቸውም፡፡ሰው በጨለማ ውስጥ
ሲጎዝ ማጅራት መቺ ከኃላው ካለ ምንም አይነት እንቅስቃሴ ሳይሰማ ትከሻዬን
ከበደኝ ይላል፡፡ያ ምን ማለት ይመስላችሆል…. እሱ ያልተመለከተውን
በጭለማ ውስጥ የተሸሸገውን አጥቂውን ጠባቂ መልአኩ አይቶት ሹክ
ብሎታል ማለት ነው፡፡እንግዲህ ያ ሰው ብልህ ከሆነ ማድረግ ያለበት
መልዕክቱን አምኖ ተፈትልኮ በመሮጥ ማምለጥ ወይም ጥቃቱን ለመመከት
እራሱን ማዘጋጀት ነው፡፡አይ ዝም ብሎ ተራ ፍራቻ ነው ብሎ የደረሰውን
መልዕክት ችላ ብሎ በእንዝላልነቱ ከገፋበት ግን ማጃራቱን ተመቶ
ይዘረራልም..ይዘረፋልም ማለት ነው፡፡
እና ለእኔ ይሄ ንስር አሞራ ጠባቂ መላዕኬ በሉት፡፡ከእናንተ ከተራ ሰዎች
በጣም የላቀ ማንነት እና ብቃት አለኝ የምላችሁ አንድም ለዚህ ነው፡፡በአካል
አብሮኝ የሚንቀሳቀስ የሚያወራኝ የማወራው ጠባቂ መልአክ ስላለኝ፡፡
የፈለግኩበት የአለም ጥግ አንጠልጥሎ የሚወስደኝ..ከሚንቀለቀል እቶን
እሳት ውስጥ ብገባ እንኳን አንጠልጥሎ በማውጣት ሀይቅ ውስጥ ጨምሮ
የሚያቀዘቅዘኝ፡፡
ካለሀሪ በረሀ ላይ ወስዶ በጥም ጉሮሮዬ ከደረቀ ከመንቁሩ ወይን አመንጭቶ
የሚያጠጣኝ…..የሲ.አይ .ኤን የስለላ መረብ በጣጥሶ የዋይት ሀውስ ራት
ግብዝ ላይ አስገብቶ የሚጥለኝ፡፡ሱፐር ሂዩማን እንድሆን ሱፐር ሆኖ ሱፐር
የሚያደርገኝ መልዐኬ ነው፡፡
በንስር አሞራ አካል ያለው የመላዕክት ነፍስ፡፡ንሰሩ ያየውን አንደማይ እና
ያሰበውን እንዳመስብ አውቃለው፡፡ልክ በአንድ ዲኮደር እንደሚሰራ ሁለት
ቴሌቪዝን በሉን….እኔ ቤቴ ቁጭ ብዬ እሱ አየሩን ሰንጥቆ በሚበርበት
የምድር ጥግ ሁሉ እያየ ያለውን ነገር ጥርት ባለምስል በአዕምሮዬ አያለው…
የንስርን አይን ደግሞ የምታውቁት ነው..እያንዳንዱ ንስውር ቅንጣት በቀላሉ
በአይኑ ሌንስ ይቀልባታል፡፡ይሄ ገለጻዬ ለብዙዎቻችሁ ግራ ሊያጋባ ይችላል፡፡
ይሄ መልአክ ነው ሰይጣን ልትሉ ትችላላችሁ፡፡መልአክ ከሆነ ለምን በእርግብ
አካል ውስጥ አላደረም ወይንም እንደተለመደው ለምን የበግ ስጋና ቆዳ
አለበሰም፡፡እሱን አላውቅም ነው መልሴ…. ደግሞም ግድም አይሰጠኝም፡፡
ዋናው በእርግጠኝነት የማውቀው ነገር የእኔ እኔነት እና የንስሩ ነፍስ የተሳሰረ
መሆኑን ነው፡፡
የኖረውን ያህል ኖሬ በሚሞትበት ቀን የምሞት እንደሆነም ይሰማኛል፡፡
ወይንም የእሱ ነፍስ ከንስር አካሉ ውስጥ ተንጠፍጥበፎ በሚወጣበት ቅጽበት
የእኔም ነፍስ ከዚህ የሰው ሰውነት ወይም አካል ውስጥ ተንጠፍጥፎ
በመውጣት ከእሱ ነፍስ ጋር በመተቃቀፍ ወደሚሄድበት ሚስጥራዊ ቦታ
አብሮት እንደሚነጉድ አውቃለው…የመዳረሻችን ፍጻሜውም የአምላክ እቅፍ
እንደሆነ ይሰማኛል ፡፡
አሁን ባለንበት ቦታ ሁለታችን ደስተኞች ነን ፡፡በዚህች ምድር ሚስጥር
እየተደመምንም ነው፡፡እርግጥ እኔ እና ንስሬ ከዚህች ምድርም አልፈን
ሌሎችንም ፕላኔቶች ለመቃኘት ሞክረናል፡፡ግን ከሁሉም ከሁሉም እንደምድር
የተዳለ እና በእግዜያብሄር ጸጋ የረሰረሰ ስፍራ አልገጠመንም፡፡
የእውነቱን ስነግራችሁ ምድር በጣም እድለኛዋ ፈለክ ነች..በህይወት
የታጨቀች..የእግዚያብሄር የመዳፍ ስራ መገለጫ ወርክ ሾፑ ነች ማለት
ይቻላል…፡፡ይሄ የሆነው ዋናው ምክንያት በፀሀይ ውስጥ የያዘችው ስፍራ
ነው… ለፀሀይ በጣም ቅርብ የሆኑ ስነ-ፈለኮች በጣም ሞቃትና በጨረር
የተጨቁ ናቸው..በዚህ ምክንያት ህይወት ሊበቅልባቸው ምቹ አይደሉም፡፡
ከፀሀይ በጣም የራቁ ፈለኮች ደግሞ በቂ ብርሀን ከፀሀይ ስለማይደርሳቸው
በጣም ቀዝቃዛ ይሆናሉ..በዚህም የተነሳ ህይወት ያለውን ነገር ለማኖር
ምቹዎች አይደሉም.. በዚህ ግን መሬት የታደለች ነች፡፡ በጣምም ያራቀች
እጅግም ያልቀረበች አራታኛውን ወይም መሀከለኛውን ስፍራ የያዘች ነች…
ስለዚህ የተመጠነ ብርሀን እና ሙቀት ነው የሚደርሳት ..በዛ ምክንያት በስነ-
ህይወት የተንበሸበሸች ነች…፡፡
ማርስ ህይወት አላት የላትም የሚባለው ክርክር ሁል ግዜ የሚነሳውና
የሚያጨቃጭቀው አንድም ከመሬት ቀጥሎ
119 views05:55
Abrir / CĂłmo
2022-07-25 22:35:33 እስኪ ተባበሩኝ ለሰው share በማረግ እ
@questions_for_all
@questions_for_all
212 views19:35
Abrir / CĂłmo
2022-07-23 19:07:18 ​​ የዳቢሎሷ ልጅ

ምእራፍ 3
.
.
.
.
....ቀኑ ተገባዶ መሽቶ ወደ መኝታዬ ስሔድ ግን ሀሳቤ ያዶት ወንዝ ላይ
እንደተጣበቀ ነበር …::እንቅልፌ ሁሉ የተቆራረጠ ..ለሊቱ የረዘመና
የተንቀራፈፈ ሆነብኝ…ክፋቱ ደግሞ ሰዓት ራስጌዬ አድርጌ ነው የተኛውት…
ተኝቼ ተኝቼ ስባንን 8፡16 ተኝቼ ተኝቼ ስነቃ 9፡34 ተኝቼ ተኝቼ ስባንን 10፡13
ተኝቼ ተኝቼ ወይኔ ተበላው ነጋብኝ ብዬ ስነቃ 11፡20 ከዛ በላይ መተኛት
አልቻልኩም፡፡
ተነሳው ሹክክ ብዬ ልብሴን ለበስሼ ሹክክ ብዬ ጄሪካኔንና ማዘያውን ይዤ
በቀስታ በራፉን ከፍቼ ወጣው..ይስፈራል…. ከጭለማው ጋር አይኔን
እስከማለማምድ ደቂቃዎች ወስደውብኝ ነበር….በጭራሮ ታጥሮ በጭራሮ
በር የተዘጋውን የጊቢያችንን አጥር መሸንጎሪያ አውጥቼ ከፈትኩና ወጣው…
ግን መቀጠል አልቻልኩም ልቤ ለሁለት ተሰነጠቀ..ሂጂ ጭግር የለውምም››
..አረ ተይ ሰው አግኝቶ ባይተናኮልሽ እንኳን አውሬስ ቢዘነጥልሽ…ከግቢያችን
መቻል በጩኃት ያንቧርቀው ጀመር…አንድ ሀሳብ መጣልኝ… ተመልሼ ወደ
ጊቢ ገባውና ወደ እሱ ሄድኩ …መጩሁን ተወና እግሬ ስር ሽብልል ብሎ
ተኛ..ቀስ ብዬ በሹክሹክታ ልክ እንደልብ አውቃ ጎዳኛ..<<አብረን እንሂድ
ተነሳ…>>አልኩትና መንገዴን ወደ መውጫው ቀጠልኩ ..ተከተለኝ..::
አዎ አሁን ቀለል አለኝ…ቢያንስ አሁን ይሻላል…….ወንዙ ጋር ስንደርስ ገና
ጭለማው እንደመግፈፍ እያለ ወፎቹ እየጩሁ ነበር…መቻል ከኃላዬ ከኃላ
ኩስ ኩስ እያለ ነው..በዛፎቹ ላይ ያሉት ወፎች የለሊ ዝማሬያቸውን
ያሰማሉ..እንደደረስኩ ጄሪካዬን አንከርፍፌ ለአስር የሚሆን ደቅቃ ፈዝዤ
ወዲህና ወዲያ አይኖቼን በማንከራተት የሆነ ነገር እፈልግ ነበር..
እንዴ ምንድነው የምፈልገው….ጄሪካኑን ይዤያለው…የወንዙም ውሀ በእግሬ
ላይ እያለፈ ወደ ፊት እየተመመ ነው..እና ለምን ጎንበስ ብዬ አልቀዳም ..?
ለምን በብርድ እንዘፈዘፋለው….አዎ መቻል ማንቧረቅ ጀመረ….. ግረ ገብቶኝ
አይኖቼን ሳቅሎጨልጭ ከወንዙ መሀል ብልቅ ብሎ ወጣ…
‹‹የፈጣሪ ያለህ..>> ጩኀቴን ለቀቅኩት.ደግነቱ የእኔ ጩኃት ከመቻል ጩኸት
ስለማይበልጥ ተውጦ ቀረ…
‹‹ዛሬም ደነገጥሽ?››
‹‹ምን አይነት ሰው ነህ…..?ቤትህ ወንዙ ውስጥ ነው እንዴ?››በመገረም
ጠየቅኩት
‹‹አዎ …ከፈለግሽ ነይ ልብስሽን አውልቂና ግቢ ….በዛውም ቤቴን
አሳይሻለው››
‹‹ቤትህን ባየው ደስ ይለኝ ነበር… ግን ዋና አልችልም››አልኩና ለቀቀልድ
ምላሽ ሰጠውት
‹‹የመና ልጅ ሆነሽማ ዋና አልችልም ብትይና አላምንም…ደሎ እንኳን ሰው
ከብቶቹም ዋና ይችላሉ››
‹‹ቢሆንም ይቅርብኝ ..ባይሆን ሌላ ጊዜ እልኩና ጎንበስ ብዬ ጄሪካኔን ወደ
ውኃ ውስጥ ከተትኩት…መቻልም ድምፅንአጥፍቶ በሜትሮች ርቀት መሬት
ላይ ለጥ ብሎ ሁለኔታችንን እየታዘበ ነው፡፡
‹‹እንግዲያው ቀረብሽ ››ብሎ መልሶ ወደ ውሀ ውስጥ እራሱን ደፈቀና
ሰመጠ ክእይታ ተሰወረ…የሆነ ነገሬን ይዞ የሄደ ነው የመሰለኝ…እንዳለኝ
ልብሴን አወላልቄ ወንዙ ውስጥ መግባት እና አበሬው መዋኘት በጣም
አሰኝቶኝ ነበር..ግን ፈርቼ ነው…በዚህ ሰእት እርቃኔን ወንዝ ውስጥ
ከማላውቀው ሰው ጋር…ግን ምን ችግር አለው…ባደረግኩት ኖሮ ቁጭት…
አንድን ነገር እኩል መፈለግ እና እኩል አለመፈለግ እንዴት ነው የሚቻለው
ከአሁን አሁን ከሰመጠበት ይወጣል ስል.. ስጠብቀው…ጄሪካኑ ሞላ..ጎትቼ
ከወንዙ ውስጥ አወጣውት እና ዳር ላይ አስቀመጥኩት….ጄሪካኔን ተሸክሜ
ጉዞዬን መቀጠል ነበረብኝ …ግን እግሬ ሊንቀሳቀስልኝ አልቻለም .ተመስገን
ነው ብልቅ ብሎ ወጣ….
‹‹ቸው በቃ ልሂድ››አልኩት
‹‹አረ ትንሽ..እስቲ ስምሽን ንገሪኝ?››
‹‹ምን ያደርግልሀል?››
‹‹ያው ቆንጆ ልጅን ስም ማወቅ ያጎጎል ..ለዛ ነው››
አፈርኩና አቀረቀርኩ
‹‹ንገሪኛ አለኝ…? በጀርባው ተንጋሎ በመዋኘት ወደ እኔ እየተጠጋ
‹‹በሬዱ››
‹‹አንቺ ቆንጆ ስምሽም ቆንጆ አሪፍ ነው››አለኝ
ፈራ ተባ እየልኩ ‹‹ያንተስ..?››አልኩት
‹‹የእኔን ሌላ ቀን ከእነ ትርጉሙ አነግርሻለው››
‹‹እንዴ ሌላ ቀን እንጋናኛለን እንዴ?››
‹‹ጥያቄዬ ማረጋጋጫ እንዲሰጠኝ የመፈለግ አይነት ነወ…››
የልብ አውቃ ነው‹‹እንዴ !!!ትቀልጂያለሽ እንዴ ..?እኔ እና አንቺ ጋና ብዙ ጊዜ
ይኖረናል …ብዙ ታሪክ እንጽፋለን››
‹‹የምን ጊዜ…?የምን ታሪክ..?››
‹‹የፍቅር ታሪክ ››
‹‹የፍቅር ….?ምን አይነት አይንአውጣነት ነው…አረ እኔ እንደዚህ አይነት ነገር
አላውቅም….››
እንደማታውቂ እውቃለው…. እኔም አላውቅም ….ግን አብረን
እንማረዋለን››ብሎኝ እርፍ
‹‹በል ይበቃሀል አሁን ልሂድ..ብዬ የግዴን ጄሪካኔን አንጠልጥዬ ተሸከምኩና
ፊቴን አዞርኩ››
‹‹በይ ደህና ዋይልኝ..ነገ በዚህን ሰዓት እጠብቅሻለው….
‹‹አታስበው…..ገን የእውነት እቤትህ እዚሁ ሳይሆን አይቀርም ››አልኩት
እየሄድኩ
‹‹አሳይሻለው ብዬሽ የለ..? አሳይሻለው…መቶ ሜትር ያህል ከራቅኩት ቡኃላ
ዞር ብዬ አየውት ደብዛው የለም…መልሶ ሰምጦ ይሆን..?ይሄ አፍዛዝ ውበት
ያለው ልጅ ሰይጣን ሳይሆን አይቀርም..?የወንዝ ሰይጣን…ግን እንዲህ
አይነት ጠንበል ሰይጣን ካለማ ይገርማል…ቤተ ክርስቲያን ግድግዳ ላይ
የተለጠፈው ስዕል ቅዱስ ሚካኤል እግር ተጨፍልቆ የሚታየወን አስፈሪውና
ሰይጣን በምስሌ መጣብኝና..ከዚህ ኛው ጋር አስተያይቼ በራሴ
አፈርኩ..በስመአብ ይቅር ይበለኝ…

ይቀጥላል....10 comment እጠብቃለሁ
282 viewsedited  16:07
Abrir / CĂłmo
2022-07-20 00:01:14 የዳቢሎሷ ልጅ

ምእራፍ


.
.
.
ይሄ አሉባልታ መነሻ ምንጩ ግልጽ እንዲሆንላችሁ ዘርዘር ላድርገው
አገራችን ደሎ የምታባል ከተማ ውስጥ እንደሆነ ነግሬያችሆለው፡ከተማዋ በጥቅጥቅ ደን የተሸፈነች ሲሆን ለሁለት የተከፈለችው ያዶት በሚባል ግዙፍ
ወንዝ ነው፡፡ያዶት ለከታማዋ ኑዋሪ ህይወት ነው…ውበት ነው….የአይን
ማረፊያቸው እና ትምክህታቸው ነው..የውጥረታቸው መተንፈሻ
ነው….የሚኮሩበት መዝናኛቸው ነው፡፡ ከተማዋ ቆላ ነች አየሩ በጣም ይሞቃል
፡፡በላብ ሚያጥብ ሙቀት.. ቀይ በንፋስ የሚበተን አፈር እና አቧራ ሲያሰቃየው
የዋለው ኑዋሪ ሀብታም ደሀ ሳይል ወደ ያዶት ይነጉዳል..ልብሱን ያወላልቅ
እና ወራጅ ወንዝ ውስጥ ይመሰጋል… እየተንሳፈፈ ይዋኛል..እንደዓሳ ብቅ
ጥልቅ ይላል…ይሄ ትልቁም ትንሹም ወንድም ሴቱም በኩልነት ያለልዩነት
የሚያደርገው ነው፡፡ሁሉም እርቃኑን በፓንት ብቻ ጎን ለጎን እየተንቧጫረቀ
መዋኘት ለእንግዳ ሚያስገርም እና ሚያስደምም ቢሆንም ለኑዋሪው ተራና
የተለመደ ደርጊት ነው፡፡
አንድ የዛ ከተማ ኑዎሪ ሌላውን ኑዋሪ ቢያንስ በዓመት አንድ ቀንም ቢሆን
እርቃኑን ወይም እርቃኖን ለማየት አጋጣሚው ይኖረዋል….የደሎ ኑዋሪዎች
ዋናተኛ ናቸው……ህጻናት የ5 አመት ጀምረው ነው ከታላላቆቻቸው ጋር
በመምጣት ዋናው መማር የሚጀማሩት..ያዶት መዋኛና ከሙቀት መቀዝቀዣ
ብቻ አይደለም..የከተማው ሰው ሁሉ ልብሱን የሚያጥበው እዛው ወዝን
ነው፡፡ሳፋውን ተሸክሞ በመምጣት ወይም ጠፍጣፋ ድንጋይ ላይ በመፈተግ..
ለከተማዋ ቧንቧ ከገባላት 10 ዓመት አይበልጠውም በእኔ የልጅነት ታሪክ
ሙሉ መጠጥም ሆነ ለምግብ ማብሰያ ውሀው የሚቀዳው ከዚሁ ያዶት ወንዝ
ነው፡፡ወሃው በአብዛኛው ሚመላለሰው በአህያ ጀርባ ነው፡ይሄንን በመስራት
የሚታዳደሩ ከሀምሳ በላይ የሚሆኑ ግለሳቦች አሉ፡፡
አህያው ላይ የእንጨት ኮርቻ ይጫናል....ኮርቻው ላይ በአንደኛው ሁለት
ባለ25 ሊትር ጄርካን በሌለኛ ወገን እንደዛው ሁለት በአንዴ አራት ጄሪካን
ወይም 100ሊትር ጭኖ ከወንዙ አንድና ሁለት ኪሎ ሜትር በማጓጓዝ
ይሸጣል፡፡ለመጠጥ የሚሆን ውሀ የሚቀዳው ግን ብዙውን ጊዜ በጥዋት ነው
ከ12 ሰዓት እስከ አንድ ሰዓት ባለው ጊዜ ነው.. የዚህ ምክንያት ያዶት ብዙ
ኪሎ ሜትሮችን ተራራዎችን ሰንጥቆ ጫካውን አቋርጦ ስለሚመጣ የሰውና
የአውሬዎች ንክኪ ሳይበዛበት ሳይደፈርስ የጠራ ውሀ ለማግኘት ነው፡፡
እና በጊዜው በዚህ ልምድ መሰረት ለቤቱ የመጠጥ ውሃ ለመቅዳት የእናቴ
ኃላፊነት ነበር..እና በለሊት ተነስቶ ወደ ያዶት በሮ በመሄድ የጠራ ውሀ ቀድቶ
ቁርሰ ቀማምሶ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ የዘወትር ተግባሯ ነበር….እና አባቴ
እና ይሄኛው የእናቴ ልምድ የሚያቆራኘው ነገር አለ፡፡
አንድ እለት እንደወትሮዋ ከእንቅልፏ ባና ጃሪካኗን አንጠልጥላ ለማዘያ
የምትጠቀምበትን ጨርቅ በትከሻዋ አድርጋ የቤቱን በራፍ ከፋታ
የግቢያቸውን የቆርቆሮ አጥር አልፋ ቁልቁል ወደ ያዶት ትነጉዳለች..ግን
ከቤቷ ብዙ ከራቀችና ከተማዋን ለቃ ወጥታ በወንዙና በከተማው መካከል
ያለውን ባዶ ወጣ ገባ ስፋራ ከደረሰች ብኃላ ነበር የሆነ ትክክል ያልሆነ ነገር
እንዳለ ያስተዋለችው…ከወትሮዋ ፈጠን ብላለች..አዎ ገና ለሊት ነበር……
ከዚህ በኃላ ያለውን ትረካ እራሶ እናቴ, ትቀጥልላችሁ..እሷ ስትጨርስ
እመለሳለው....
የተወሰነ ፍራቻ ቢሰማኝም ወደ ኃላዋ አልተመለስኩም የባሀርዛፍ ደን ያለበትን
ምንገድ ሰንጥቄ ሳልፍም ከነፍራቻዬ ነኝ..ወደ ኃላዬም ሆነ ወደ ፊት ለፍቴ
እየተሸከረከርኩ ብገላመጥ ምንም የሚታይ የሰው ዘር አላየውም… በደን
ወደተሸፈነው የወንዙ ድንበር ስደርስ ጉሬዛዎች ከዛፍ ወደዛፍ እየተንጠላጠሉ
ሲዘሉ አያለው …ያዶት ሾሾሾሸሸ ብሎ ሲፈስ ከሩቅ ይሰማል..ደረስኩና
ቀሚሴን በመጠኑ ሰብስቤ ወደወንዙ አንድ ሜትር ያህል ጋባ ብዬ ጄሪካውን
መሙላት ጀመርኩ..ግማሽ እንደደርሱክ ከወንዙ መሀለ የሆነ የሚንቦጫረቅ
ድምጽ ሰማውና አውሬ መስሎኝ ጄሪካኔን ጥዬ በርግጌ ከወንዙ ወጣውና
እራቅ ብዬ ስመለከት….እኔ ጥዬ የወጣውት ጄሪካን በውሀው ግፊት ወደ
መሀል ተምዘግዝጎ አውሬ ወደመሰለኝ አካል ሲጓዝ ተመለከትኩ… ደግነቱ
ሰማውት ድምጽ የአውሬ ሳይሆን የሰው ነው፡፡መጀመሪያ ዕርቃኖን የምትዋኝ
ሴት መስላኝ ነበር..
አስተውዬ ና ተረጋግቼ ሳስተውል ግን ቀይ ጥቅልል ጥቁር ፀጉር ያለውና
በውሀው ለስልሶ ግንባሩ ላይ ድፍት ያለበት የሆነ የአማልክት አይነት መልክ
ያለው ልጅ የእኔን ጄርካን ይዞ በፍራቻዬ እየሳቀብኝ ተመለከትኩት….
‹‹ይህን ያህል ፈሪ ከሆንሽ በዚህ ሰዓት ለምን መጣሽ››
‹‹የነጋ መስሎኝ ነዋ ..አንተስ በዚህ ለሊት ምን ትሰራለህ››
‹‹እኔማ አንቺ እንደምትመጪ አውቄ እየጠበቅኩሽ ነው››
‹‹የት አውቀህ ነው የምትጠብቀኝ››
እርግጥ አላውቅሽም ግን ውሀ ልትቀጂ በለሊት ስትመጪ ሁሌ
አይሻለው››አለኝ ከወንዙ መሀል እኔ ባለውበት አቅጣጫ ወደ ዳር ቀረብ
እያለ››
‹‹አንተ ሁል ጊዜ ለሊት እዚህ ምን ትሰራለህ››
‹‹እቤቴ እዚሁ ቅርብ ነው… በዚህ ሰዓት መዋኘት ያስደስተኛል…ከያዶት ጋር
ሚስጥር የምናወራው በዚህ ሰዓት ነው…እያንዳንዱን አዲስ ቀን በደስታ
የምቀበለው እዚሁ ሆኜ ነው››
‹‹በል እሺ ጀሪካኔን ስጠኝና ዉሀዬን ልቅዳ ››አልኩት..ከማላውቀው ሰው ጋር
በአጉል ሰዕት አጉል ቦታ ሆኜ ከዚህ በላይ ማውራት አስፈሪ ቢሆነብኝም
ጄሪካኑን ግን እውነት እንዳልኩት እንዲመልስልኝ አልገፈለኩም ..‹‹ልቅዳልሻ…
እስከዛ አንቺ አውሪኝ››ብሎ ጄርካኑን በሁለት እጆች ወደታች የውሀው ጥልቃት
ደፍቆ. ዶዷዷዷ በሚል ድምጽ በመተጀብ መሙላት ጀመረ
‹‹አውሪኛ እስክሞላልሽ››
‹‹ምን ላውራህ››
‹‹አሁን ብጠልፍሽስ››
‹‹ጠልፈህ ምን ታደርገኛለህ››
‹‹ተጠልፎ ምንድነው የሚደረገው..አገባሻለዋ››
‹‹ሆሆይ…ጠልፎ ማግባት እንዲህ ቀልድ ሆነ እንዴ..አረ ቶሎ ሙላና ስጠኝ
ልሂድበት››
ቀስ በያ…ቆንጆ ስለሆንሽ እኮ ነው ልጥለፍሽ ያልኩሽ››
‹‹የምለው ጠፋኝ..ለመሆኑ እቤቴ ቅርብ ነው ምትለኝ እዚህ ቅርብ ከጫካ እና
ከጅብ ጉድጎድ በስተቀር ምን ቤት አለ..››
‹‹እውነቴን ነው የእኔ ቤት እዚሁ ቅርብ ነው…ግን በአይን አይታይም…ፀባይ
ካለሽ አንድ ቀን ወስድሻለው››
‹‹አረ ይቅርብኝ….ብዬ ከወንዙ አውጥቶ ያቀበለኝኝ ጀሪካኔን በጀራባዬ አዝዬ
እየተእሱ ግማሽ አካሉን ወንዝ ውስጥ ግማሽ አካሉን እርቃኑን ደግሞ አጋልጣ
ለኔ እያስጎበኘን በአይኖቹ ሸኘኝ..እኔም እየተገላመጥኩ ወደ ፌት በመንደርደሬ
አመለጥኩ በሚል እፎይታ ግን ደግሞ ትንሽ ብቆይስ…ትንሽ ራሽ በሚል
ቁጭት ወደ ቤቴ..እቤት ስደርስ ሰዓቱ ገና ለአስራ ሁለት ሰዓት እርብ ጉዳይ
ነበር…ሁለተኛ ሰዓት ሳላይ .ንቅንቅ አልልም..1፡30 መሆኑን ሳላረጋግጥ
ንቅንቅ..ቅዱስ ሚካኤል ነው ከመአት ያወጣኝ …ብዬ ፎከርኩ..ጥፋቴን
ላለመድገም ለራሴ ቃል ገባው፡፡

ይቀጥላል.... እንዲቀጥል 10 comment
309 viewsedited  21:01
Abrir / CĂłmo
2022-07-18 20:25:03 የዲያቢሎሷ ልጅ

ምእራፍ


.
.
.
.
ሚሥጥር ማነፍነፍ፤የሠውን ገበና መበርበር፤የወዳጆችን
ሹክሹክታ መጥለፍ ዋና ባህሪዬ ነው።ከምግብ እኩል
ሚሥጥር ነው የሚያኖረኝ።በተለይ በትልልቅ ነጋዴዎች
መካከል የሚደረግ ሚስጥራዊ ድርድር...በፓለቲከኞች
መካከል ከመጋረጃ ጀርባ የሚካሄድ ድርድር ማነፍነፍ
የተፈጠርኩበት ዋና የህይወቴ አላማ ነው።
ይህ አብሮኝ የተወለደ በተፈጥሮ የተሠጠኝ ችሎታ ቢሆንም
እኔ ደግሞ በተለያዩ መንገዶች አሣድጌዋለሁ አዳብሬዋለሁ...
ለምሣሌ በወንጀልና ሥለላ ላይ የተጻፉ መጽሀፎችን ማንበብ
ፊልሞችን መመልከት...በየእለቱ የምከውናቸው ተግባራት
ሢሆኑ ለዚህ እንዲረዳኝ በቂ የሆነ ወታደራዊ
ሥልጠና፤የሥለላ ጥበብ እና ጠለቅ ያለ የኮምፒውተር
እውቀትን ገብይቻለሁ...አሁን 32 አመቴ ላይ ነኝ።ይሄንን
በእቅዴ አሥገብቼ ዝግጅት ማድረግ የጀመርኩት ከ17 አመቴ
ጀምሮ ነው።
እሥቲ ፈታ አድርጌ ላሥረዳችሁ ልጅ ሆኜ ጀምሮ አንድ ሠው
ሢያወራ እኔ ማዳምጠው ሠውዬው በቃላት ከሽኖ
የሚያሥተላልፈውን መልእክት ሣይሆን በሚናገራቸው
ቃላቶች አድበሥብሶ ወደ ውሥጡ ያሥቀራቸውን እና
የደበቃቸውን ቃላቶች ተሠብሥበውና ተገጣጥመው አንድ
ላይ በመጣመር የሚያሥተላልፉትን መልእክት ነው።እኔ
ማዳምጠው ሥሜቱን ነው..የፊቱ ቋጠር ፈታ ላይ
የሚነበበውን መልእክት ነው..በዛ ደግሞ ከማንም ጋር በነፍሴ
እንኳን ቢሆን አሥይዤ መወዳደር እችላለሁ...ሊነክሠኝ
የመጣንና ሊሥመኝ የመጣን ሠው ገና በኪሎ ሜትሮች ርቀት
ነው መለየት የምችለው...በተለይ ማወቅ ፈልጌ ትኩረቴን
ሠብሥቤ ትንሽ ካውጠነጠንኩ በቃ የሆነ መንፈሥ አየሩን
ሠንጥቆ በመምጣት ሚሥጥሩን በጆሮዬ ሹክ ይለኛል...
ለነገሩ ሁሉ ነገሬ ከሠው የማይገጥም እና የተለየ የሆነው ገና
ከውልደቴ ጀምሮ ነው።
የተወለድኩት እንደማንም የሠው ልጅ በዘጠኝ ወሬ
አይደለም..አንድ አመት ከሥድሥት ወር በእናቴ ማህጸን
ውሥጥ ዘና ብዬ ኖሬያለሁ...ምን አልባት በሠው ልጅ
የህይወት ታሪክ በእናቱ ማህጸን ከበቂ በላይ ለሆነ ጊዜ
በመንደላቀቅና በምቾት በመኖር ሪከርዱ በእጄ ሣይሆን
አይቀርም..እርግጥ ብዙዎቹ ይሄንን ታሪክ ሢሠሙ
ባለማመንና በመጠራጠር ክርክር ውሥጥ ይገባሉ<...እናትሽ
አንቺን የፀነሠችበትን ቀን ተሣሥታ ነው>የአብዛሃኞቹ መላ
ምት ነው..ግን ይሄ እንዳልሆነ ከመጀመሪያ ሣምንት የጽንሠቷ
ጊዜ አንሥቶ እሥክትገላገል ድረሥ የሀኪም ክትትል ውሥጥ
ሥለነበረች ትርክቴ በሳይንሥ መረጃ የተደገፈ ነው..ይሄም
በተወለድኩበት ሣምንት በኢትዮጵያ ሬድዮ የቀትር ዜና ላይ
<<በባሌ ክፍለሀገር በደሎ መና ከተማ ኑዋሪ የሆነችው በሬዱ
ዲንቃ የምትባል ወጣት ሤት በአንድ አመት ከሥድሥት ወሯ
ጤነኛ የሆነች ሤት ልጅ መገላገሏን ከከተማው ጤና ጣቢያ
በደረሠን ዜና ማወቅ ተችሏል።....>>የሚል ዜና ተነግሮ
ሥለነበር ከመወለዴ የከተማዋ ዝነኛ እና ታዋቂ ሆኛለሁ።
አይዟችሁ ገና አትገረሙ።እራሤን ችዬ መቀመጥ የጀመርኩት
በሶስት ወሬ ነው...በሥድሥተኛ ወሬ መራመድ ጀመርኩ
በአንድ አመቴ እቤታችን ውሥጥ በእኩል ደረጃ ይነገሩ
የነበሩትን አማርኛ እና ኦሮምኛ ቋንቋዎችን አቀላጥፌ ማውራት
ቻልኩ።
ይሄ ሁኔታዬ ሠው ሁሉ እንዲፈራኝ እና እንደሌላ ፍጡር
እንዲቆጥረኝ አደረገ።እኔ ሣሥብ ያው በአንድ አመት
ከሥድሥት ወር እናቴ ማህጸን ሥቆይ ብዙ ነገር ተምሬ
ብዙውን ነገር እዛው ጨርሼ የወጣሁ ይመሥለኛል...ያ
ማለት በዘጠኝ ወራቸው የሚወለዱ የሠው ልጆች
እድገታቸውን ሣይጨርሡ ማወቅ የሚገባቸውን ጠንቅቀው
ሣያውቁ፤እራሣቸውን የመርዳት አቅሙን ሣያዳብሩ ቸኩለው
እንደሚወለዱ ፍንጭ የሚሠጥ ክሥተት ነው።....አዎ
እውነቴን ነው ለምሣሌ ከሠው ልጅ ውጭ ያለ ሌላ
እንሥሣት ተመልከቱ...ገና ከመወለዳቸው በራሣቸው
ለመቆም ይፍጨረጨራሉ..በቀናት ውሥጥ የራሣቸውን
ምግብ በራሣቸው ቃርመው መመገብ ይጀምራሉ።
ከእናታቸው የሚፈልጉት የተወሠነ የደህንነት ጥበቃ
እንድታደርግላቸውና መንገድ እንድታሣያቸው ብቻ
ነው...የሠው ልጅ ግን ልፍሥፍሥ ነው...በእናቱ ማህጸን
ዘጠኝ ወር አሣልፎ ከተወለደ በሁላ ሌላ ዘጠኝ አመት እናቱ
ጉያ ውሥጥ ተወትፎ በመነፍረቅ ሢልወሠወሥ ይገኛል..በሃያ
አመቱ እንኳን እራሡን ችሎ ከቆመ ጠንካራና ጀግና ተብሎ
ይሞገሣል...ሠው ራሡን ለመቻል ለሃያ ረጂም አመታት
ማደግ..መማር..መሠልጠን..መጠንከር ይጠበቅበታል።እኔ
ግን እንዲ እንዳልሆንኩ ገና በጥዋቱ ነው
የማውቀው...ይቅርታ የኔ ልዩ መሆን ከውልደቴ ነው
የሚጀምረው ብያችሁ ነበር አይደል ተሣሥቼያለሁ...ከጽንሠቴ
ነው የሚጀምረው..ከአባቴ ማንነት...እናቴ የአባቴን ማንነት
አታውቀውም።አታውቀውም ሥላችሁ እንዲሁ ድንገት
ከደፈራት ሠው..ወይም ባጋጣሚ ወሲብ ከፈጸመችው ሠው
ጸነሠችኝ እያልኳችሁ አይደለም።በጣም ካፈቀረችው..በጣም
ከወደደችው..በጣም ካመለከችው ሠው ተኝታ ነው
የጸነሠችኝ...<<ግን ሥለዚህ ሠውዬ ሥታወራ
....ሥለመልኩ ሥትደሠኩር ..ሥላሣለፉት የፍቅር ታሪክ
ሥትዘምር በልዩ መደነቅና በከፍተኛ ኩራት ቢሆንም ታሪኩን
ከሚያደምጧት ሠዎች መካከል 99.9 ፐርሠንቱ
አያምኗትም...ሠው ሣይሆን ጋንኤል ነበር ያፈቀረችው
ይሏታል..
ከዛም አለፍ ብለው ያፈቀረችው ብቻ ሣይሆን የጸነሠችውም
ከዛው ጋንኤል ነው ብለው ይደመድማሉ...ይሄ ሀሚት
የሚጀምረው ደግሞ ከገዛ ዘመዶቿ ነው..ከዛ ጎረቤቶቿ
ተቀበሉ እና ለከተማው ነዋሪዎች በተኑት...
ከጋንኤል ለመጸነሷ ማሥረጃችን ብለው የሚያቀርቡት
እንደሠው በዘጠኝ ወር መውለድ አለመቻሏ ከዛም
አልፎ...ከእሷ የተወለድኩት እኔ ልጇ የጋንኤልን ጉልበትና
ጥንካሬ ይዤ መወለዴን በመተንተን ማሥረጃቸውን
ያጠናክራሉ...ሥለዚህ እንደ እነሡ እምነት የእኔ ልዩ ብቃት
ምንጩ ከጋንኤሉ አባቴ ዲ.ኤን.ኤ የወረሥኩት እንደሆነ
እርግጠኛ ናቸው...የቅርቤም ሆኑ የሩቆቹ ሠዎች ይሄንን
አንሥተው ሢያንሾካሽኩ ድንገት ሥደርሥባቸው የሠማዋቸው
ሢመሥላቸው የምበሣጭና የምሸማቀቅ ይመሥላቸውና
ይደነግጣሉ....እኔ ግን እንደውም ኩራት ነው
የሚሠማኝ...አጠገቤ ሢሆኑ በጣም ትንሽነት
ሥለሚሠማቸውና ደካማነታቸውን ሥለማጎላባቸው
ከሚሠማቸው የበታችነት ሥሜት ለመላቀቅ የፈበረኩት ዘዴ
አድርጌ ነው የምወሥደው።እውነትም ቢሆን ደግሞ ግድ
የለኝም...ሠውና ጋንኤል ሢዳቀል እኔን የመሠለ በልዩ
ችሎታና ሀይል የተሞላች ሠው ማለቴ ሠው እና ጋንኤል
ማሥገኘት ከቻለ..
ጥሩ ነዋ።የሥነ ህይወት ተማራማሪዎችሥ በዳርዊን ቲዎሪ
በመመራት የተሻለ ጥራት ያለው ዘር ለማግኘት አይደል ሁለት
የተለያየ ዘር አዳቅለው በማዋሃድ ሌላ የተሻለ ዘር ለማግኘት
ሢጥሩ የሚታዩት(አንዳንዴ ውጤቱ በተቃራኒው ቢሆንም)....

ክፍል 2 ይቀጥል የምትሉ 5 comment ፃፉልን ስለ ታሪኩ
279 viewsedited  17:25
Abrir / CĂłmo
2022-07-15 13:18:10 ​​​​ ♂የሰፈሬ ልጅ

እውነተኛየፍቅርታሪክ

የመጨረሻው ክፍል

... ጉዴን ይነግረኝ ጀመር ቢኒ ወደ ጢስ አባይ አጎቴ ጋ እሄዳለው ያለኝ አውቆ እንደሆነ እና
እናቴ ዘንድ ወደ አ/አ እንደ ሄደ እናቴ ደማነስ ስላለባት በጣም ታማ ስለነበረ እሷ ሊያያት እንደ ሄደ ነገረኝ ድብስ ብስ አድርጎ ተናግሮ ማለፍ ፈለገ እኔም በጣም ገረመኝ አንድ ጥያቄ የፈጠረብኝ ነገር አለ አልኩት ቢኒ ይሄን ታክል ለእናቴ መስዋትነትን የከፈለ ለም
ንድን ነው አልኩት ያን አላውቅም አለኝ ምን አልባት ሰለሚወድሽ ይሆናል አለኝ በዚህ ዘመን ምን አይነት ፍቅር ነው"" ይሄን ታክል መስዋትነት የሚያስከፍል አልኩኝ አቤል እውነቱን ልንገርህ አደለ ላለመናገር ስለፈለክ እንጂ የሆነ ሚስጥር እንዳለ ይገባኛል አልኩት እንደዛ ለምን ታስብያለሽ እያለ ብዙ ቀባጠረብኝ እንደ ማይነግረኝ ሳውቅ አመሰግናለሁ በቃ ቻወ አልኩት ለተወሰነ ሰከንድ ዝም አለኝ

ማውቅ የለለብሽን ባታውቂ ምን ይቀርብሻል አለኝ ሚጠቅመኝን አኔነኝ ማውቅ አልኩትኝ አሺ በቃ ሰረኬን ጠይቂያት አለኝ ሰርኬ ማለት ሰራተኛችን ናት አሁን የባሰ ደነገጥኩ እንነዚህ ሰዋች ቢኒ እንዴት አድርጎ ቢቆልፋቸው ነው ይሄን ታክል ለመናገር የከበዳቸው አልኩኝ እሺ ብዬ ተሰናብቼው ተለያየን ሰራተኛችን በሌላ ቀን ማታ ላይ ብዙ ስናወራ ቆየንና ከብዙ ጭቅ ጭቅና ንትርክ በኃላ ቢኒ ይሄን ሁሉ ሊያደርግ የቻለው የቢኒ እናት ለእናትሽና ለአባትሽ መለያየት ዋና ምክንያት ናት አለችኝ ደነገጥኩኝ የቢኒ እናት በጣም ክፉና ወረኛ ሰለነበረች ለእናትሽ ሰለአባትሽ መጥፎ ነገር እየተናገረች እንዲፋቱ ያደረገች እሷ ናት አለች ከዚያን በኃላ አባትሽ ታሞ ስለ ነበረ ብዙም ሳይቆይ እንደ ሞተ እና እናቴም የአባቴን መሞት ስትሰማ ከዛን ቀን ወዲህ በሽተኛ እንደሆነች ብዙ ስቃይ እንዳሳለፈች በሰአቱ ገና ህፃን እንደ ሆንኩ ነገረችኝ ቢኒ ይሄን ሁሉ ሰለ ሚያውቅ እናቱ ጋር ተጣልቶ አባቱ ጋር እንደ ሚኖር እና እናቴ የሞት አፋፍ ላይ ሁና ታማ እንኩላሊቱን እንደ ሰጣት በተለያየ ግዜ ደግሞ ደማነስ ስላለባት ደሙን እንደ ሰጣት ነገረችኝ ይሄን ሁሉ ያደረገው እናቱ የበደለቻትን እሱ ሊክሳት እንደ ሆነ እኔንም ሰለሚወደኝ ይሄን ሁሉ እንዳደረገ ስትነግረኝ የሰማሁትን መቀበል አቃተኝ በእንባ ታጠብቁ ቢኒ የልጅ አዋቂ ነው እድሜውና አስተሳሰቡ አይገናኝም ብህይወት እስካለሁ ድረስ ቢኒን እንደ ምጠብቀው ለራሴ ቃል ገባሁ።

ከብዙ ልፋት በኃላ እኔም በጥሩ ውጤት ተመረኩኝ ወድሜ በጣም ደስ አለሁ ህይወት ቀጠለች ስለ ቢኒ ሳልስማ አመታት አለፈኝ እሁድ ቀንን አወደዋለሁ ጉዋደኞቼ ጋር ስንዝናና ውለን ወደ ቤት መጣሁ
ሰራተኛችን ሳያት ተኝታለች እኔም ልረፍ ብዬ ወደ ሩሜ ስሄድ
ለስለስ ያለ ሙዚቃ ተሰማኝ ወደ ክላሴ የምሄድበት ኮሪደር እንደ ጨፌ የተጎዘጎዘ ቀይ ፅገሬዳ አየሁ የልቤ ምት ሲጨምር ይታወቀኛል ቀስ ብዬ በሩን ከፈትኩት በህይወቴ ብዙ ሚያምሩ ክለሶችን አይቻለሁ እንደ ዛሬው ግን የሚያምር ክላስ አይቼ አላውቅም ወደ ወስጥ ገበሁ ሳለሰስበው ከኃላዬ አይኔን ከደነኝ ድምፁን ጎርነን አደርጎ እኔ ማነኝ አለ ቢኒ ነው ከደስታዬ ብዛት የተነሳ ጨውኩኝ ተጠመጠምኩበት
ብዙ ግዜ አልቅሻለሁ እንደ አሁን ግን የደስታ እንባ አላለቀስኩም
በቃ ቢኒ ማለት ለእኔ ወንሜ እህቴ እናቴ አባቴ ጓደኛዬ ፍቅረኛዬ ነው በህይወቴ አልሜው የማለውቀውን ነገር አደረገለኝ የእናቴን ቀለበት አሰረልኝ ከዚህ በላይ ፍቅር የት አለ ለቢኒ አረገዝኩለት ህይወት ትቀጥላለች ። አንድ የምወደው የመጽሀፍ ቅዱስ ቃል አለ

#በለሱንየጠበቀፍሬውንይበላልጌታውንየጠበቀይከብራል

እናንተም ከእኔ ህይወት ብዙ እንደ ተማራቹ ተስፋ አደርጋለሁ!!

//ተፈፀመ//


ምስጋና
ታሪኩን በመከታተል አስተያየታችሁን ላደረሳችሁኝ በሙሉ!

በታሪኩ ላይ ያላችሁን አስተያየት ከታች አስተያየት comment የሚለውን በመንካት ያድርሱን፡፡
​
. ꧁༺༒༻꧂
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share ◉●••

┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄

LℐᏦℰ Ꭿℕⅅ ЅℋᎯℛ★彡
308 views10:18
Abrir / CĂłmo
2022-07-11 23:12:05 ​​​​ ‍ የሰፈሬ ልጅ

እውነተኛ የፍቅር ታሪክ

#ክፍል_14

... የወንድሜ ትክሻ ላይ የእናቴን ልብስ አየሁት እናቴ ሞተች ከዛን በኃላ የተፈጠረውን አላውቅም ከሁለተ ቀን በኃላ ራሴን ሆስፒታል አገኘውት
በቃ የተፈጠረውን ሳውቅ አበድኩ የእናቴ መቃብር ላይ እንዴት ልቁም ህይወቴ ምስቅልቅሉ ወጣብኝ እናቴን ዳግም እንደ ማላገኛት ሳውቅ መኖር አስጠላኝ ወንድሜ ከእልቅሶ ብዛት ማውራት አይችልም ሀዘኔ በጣም በረታ ሁሉም ነገር እንዳያልፍ የለ አለፈ

በጣም የሚገርመው ቢኒ ወደ አጎቱ ከሄደበት ቀን ጀምሮ አላየሁትም እናቴ ከሞተች አንድ ወር አለፈው ወንድሜ ለእኔ የካናዳ ፓስፖርት አምጦ ሰጠኝ ደነገጥኩኝ ፕሮሰሱን ከጀመረ ቆይቷል ግን በዚህ ሰአት ያመጣዋል ብዬ አላሰብኩም ወንድሜ ቤታችንንም ሽጦታል ሰራተኛችን አሳዘነችኝ ከህፃንነቴ ጀምሮ አሷ ናት ያሳደገችኝ እናቴን አጥቻት ሰራተኛችንን አጥቻት ቢኒን አጥቼው መኖሬ አስጠላኝ በቃ ምርር ብዬ አለቀስኩኝ ወንደሜን አልሄድም አልኩኝ እንደዛ ስለው ከእኔ በላይ አበደ አውቃለሁ ካሁን በኃላ ያለኝ በቸኛ ተስፋዬ ወንድሜ ነው ይሄን ሀሳብ ደግመሽ እንዳታስቢው አለኝ ለመብረር ሁለት ሳምንት ሲቀረን ወደ አ/አ መሄድ አለብን አለኝ ልቤ በፍረሀት ተውጧል ሰፈረ ላይ አቤልን አገኘውት ቢኒን ስጠይቀው እንዳላየው ነገረኝ መናገር አልፈለገም በቃ ስለ ቢኒ ከአቤል ውጭ የሚያውቅ የለም ቢኒን የማግኘት ተስፋዬ መነመነ ሳቄ ሁሉ ሀዘን ዋጠው

ወደ አ/አ ልንሄድ ሰንል ዕቃችንን ስናወጣ ሰራተኛችንም ቦርሳዋን አወጣች ደነገጥኩ አንቺ ወንዴት ልትሄጂ ነው አልኳት እየሳቀች የእጅ ቦርሳዋን ከፍታ ፓስፖርቷን አሳየችኝ ዘልዬ ተጠመጠምኩባት
እናቴ እኔ ጋር የምትሄድ ያህል ነው የተሰማኝ ደስ አለኝ ወንድሜን ሂጄ አቀፍኩት በጣም አመሰገንኩት ለእሷም የካናዳ ፕሮሰስ ጨረሰላት
በቃ ሰፈሬን ስለቅ ውስጤ ተረበሸ ቢኒን ሳስበው እንባዬን አልቻልኩም

ያለፈው ሁሉ አልፎ ካናዳ ቶሮንቶ ገባን ወንድሜ ከናዳን ይወዳታል ለብዙ አመታት ኑሮባታል እኔ ግን ሀሳቤ ቢኒ ጋ ነው ቢኒ ከህይወቴ ለአንድ ሰከንድ መጥፋት አልቻለም እሱን የማላስበብት ግዜ የለኝም
ከብዙ ግዜ በኃላ አቤልን ዋትሳፕ ላይ አገኘሁት በጣም ደስ አለኝ በቃ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ነው የማገኘህ እውነቱን ምትነግረኝ ከሆነ ምንም ሳትደብቀኝ ንገረኝ አልኩት እኔ እንደዛ ስለው እንደ መደናገጥ ቢልም
ጉዴን ይነግረኝ ጀመር ቢኒ ወደ ጢስ አባይ አጎቴ ጋ እሄዳለው ያለኝ አውቆ እንደሆነ እና
እናቴ ዘንድ ወደ አ/አ እንደ ሄደ…

የመጨረሻው ክፍል

​
. ꧁༺༒༻꧂
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share ◉●••

┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄

የመጨረሻው ክፍል እንዲለቀቅ 15 comment እጠብቃለሁ።..ቶሎ 15 comment ከሞላ ይለቀቃል
344 viewsedited  20:12
Abrir / CĂłmo
2022-07-07 08:40:07 ​​​​ ♂የሰፈሬልጅ

እውነተኛየፍቅርታሪክ

ክፍል13

... ወደ ክላሴ ስሄድ የሆነ ጠረን አፈጫዬን ሲያውደኝ ይታወቀኛል ክላሴን ስከፍተው በፅገሬዳ አበባ ተሞልቷል ቢኒ ነጭ በነጭ ልብሶ ፊት ለፊቴ ቁሟል ሳየው ደነገጥኩኝ ዘልዬ ተጠመጠምኩበት በጣም ደስ አለኝ ድጋሚ የህልም አለም እስኪ መስለኝ ድረስ የምናፍቀውን ምሽት ከሱ ጋር አሳለፍኩ በህይወቴ እድለኛ እንደ ሆንኩ አሰብኩ


ከሳምንት በኃላ ቢኒ አጎቱን ጥየቃ ወደ ጢስ አባይ ሄድ ከሁለት ቀን በላይ ግን ሳላየው ማደር አልቻልኩም በጣም ናፈቀኝ እኔም ሳልነግረው እሱ ዘንድ ሄድኩ አጎቱ ደስ ይለኛል ከአንዴ ሁለቴ ሂጃለሁ ልድረስ አከባቢ ስል እትዬ እስካል የምንላት የሰፈራችን ሴትዮ ደወለችልኝ ልቤ ደነገጠ ሄሎ ስላት የሆነ ጫጫታ ይሰማኛል የትነሽ ቶሎ ነይ ወደ ሰፈር አለችኝ ድነጋጤዬ ከቀድሙ ይባስ ልቤ ይመታ ጀመረ ምንድ ነው ስላት ስልኩን ዘጋችብኝ ወደ ሰራተኛችን ብደውል ስልኳ አይሰራም የቤቱም ይጠራል የሚያነሳው የለም በቃ ውስጤ ተረበሸ ለማን ልደውል ማሰብ አቃተኝ እንደምንም ብዬ ወራጅ አለ ብዬ ወረድኩ መጓዝ አቃተኝ ምን እንደ ተፈጠረ አላውቅም ትንሽም ቢሆን በህፃንነቴ ጀምሮ ልብ ድካም አለብኝ እንደምንም ብዬ መጓዝ ጀመርኩ ወደ ከተማ የሚሄድ መኪና ሁሉ የሞላ ነው መጨረሻ ላይ አንድ የመስክ መኪና ቆመልኝ

ሴት ናት ሹፌሩዋ ተጫዋች ናት ከተማ እንደ ደረስኩ ባጃጅ ኮንትራት ይዤ ወደ ሰፈር ሄድኩኝ ሰፈረ ልደርስ ስል ሰው ነጠላ ለብሰው
ወደ ሰፈራችን እየገቡ ነው ውስጤ በፍረሀት እየተንቀጠቀጠ ነው
ወደ ሰፈር መታጠፍያው ስደርስ አቁም አልኩኝና በእግሬ መሄድ ጀመርኩ በርቁ ከእኛ ቤት ላይ ብዛት ነጠላ የለበሰ ሰው ይታየኛል
ጩኀት አለ #አምላኬእባክህንብርታቱንስጠኝአልኩኝ
እየተጠጋሁ ስመጣ እኛ ቤት ላይ ነው ሀዘን ማን ሞተ ብዬ ደነገጥኩ ከሩቅ ሲያዩኝ እነ አቤል እየተሯሯጡ መጡ
መጓዝ አቃተኝ ሰራተኛችን ከሩቅ የሆነ ፎቶ ይዛ ያዙኝ ልቀቁኝ ትላለች በመኃል የወንድሜ ትክሻ ላይ የእናቴን ልብስ አየሁት…

ይቀጥላል...

✎ ክፍል 14

​
. ꧁༺༒༻꧂
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share ◉●•

┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄

LℐᏦℰ Ꭿℕⅅ ЅℋᎯℛ★彡
ቀጣይ part 14 እንዲለቀቅ የተሰማችሁን 10 comment እጠብቃለሁ።
422 views05:40
Abrir / CĂłmo