Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን 4 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ማስገባቱ ተገለፀ! በሀገሪቱ ያለው | YeneTube

የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን 4 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ማስገባቱ ተገለፀ!

በሀገሪቱ ያለውን ገበያ ዋጋ ለማረጋጋት የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን 8 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ለማስገባት አቅዶ በመጀመሪያው ዙር 4 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ማስገባቱ ተገለፀ።ከውጭ ሀገር ከ11 ቢሊዮን ብር በላይ ተገዝቶ የገባው ይህ ስንዴ በአምስት ማዕከላት ማለትም በአዲስ አበባ፣ በሻሸመኔ፣ በባህርዳር፣ በአዳማ እና ድሬዳዋ በሚገኙ ማሰራጫ ማዕከላት ይሰራጫልም ሲሉ የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አቻ ደምሴ አስታውቀዋል። በተለያዩ ዳቦ ቤቶች የሚታየውን የዋጋ ጭማሬ እና የዱቄት እጥረት በመቅረፍ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ይደረጋልም ብለዋል።በሚቀጥሉት 15 ቀናት ስርጭቱ በማዕከላቶቹ የሚከናወን ሲሆን የሚሰራጨው ስንዴ በአግባቡ ጥቅም ላይ መዋሉን ቁጥጥር ይደረጋልም ተብሏል።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa