Get Mystery Box with random crypto!

እንደ ቀድሞ ቅኝ ገዥዎቻቸው ወደ ደቡብ አፍሪካ የጉዞ ገደብ ያደረጉ የአፍሪካ ሀገራት ዉሳኔ ያሳዝና | YeneTube

እንደ ቀድሞ ቅኝ ገዥዎቻቸው ወደ ደቡብ አፍሪካ የጉዞ ገደብ ያደረጉ የአፍሪካ ሀገራት ዉሳኔ ያሳዝናል ሲሉ ራማፎሳ ተናገሩ!

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሀገራት የሚደረገውን ጉዞ በመገደብ የምዕራባውያን ድርጊት የተከተሉ የአፍሪካ ሀገራትን ተቃዉመዋል፡፡ራማፎሳ የሚያሳዝን ዉሳኔ ነው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ኦሚክሮን በደቡብ አፍሪካ መገኘቱን ተከትሎ እንደ ቀድሞ ቅኝ ገዥዎቻቸው ወደ ደቡብ አፍሪካ ጉዞን የከለከሉ የአፍሪካ ሀገራት እንዲህ ዓይነት ዉሳኔ ባይወስዱ ይመረጥ ነበር ሲሉ ራማፎሳ ተናግረዋል፡፡በርግጥ እኔንም ያሳስበኛል ደግሞም ለእነሱ አክብሮት አለኝ ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

አፍሪካን ለመዝጋት በጣም ፈጣን እንደነበሩት እንደቀድሞ ቅኝ ገዥዎቻችን ምላሽ ባይሰጡን ኖሮ ዉይይትን እንመርጥ ነበር ሲሉ ራማፎሳ ተናግረዋል፡፡ሩዋንዳ፣ ሲሸልስ፣ ሞሪሸስ፣ ግብፅ እና አንጎላ ድንበራቸውን ወደ ደቡብ አፍሪካ ሀገራት ከዘጉ የአፍሪካ ሀገራት መካከል ተጠቃሽ ናቸው።

የኦሚክሮን አዲስ ልዉጥ ቫይረስ በደቡብ አፍሪካ መገኘቱን የአለም ጤና ድርጅት ሪፖርት ካደረገ በኃላ በበርካታ ሀገራት ዉስጥ ተጠቂዎች እየተገኙ ይገኛል፡፡ደቡብ አፍሪካ በራሷ እና በአጎራባች ሀገራት ላይ የተጣለውን የጉዞ ክልከላ ፍትሃዊ ያልሆነ እና ሳይንስን መሰረት ያላደረገ ስትል ታወግዛለች።

[ዳጉ ጆርናል]
@YeneTube @FikerAssefa