Get Mystery Box with random crypto!

​​✟✞✟አላፍርም እኔ በማርያም✟✞✟ አላፍርም እኔ በማርያም አላፍርም እኔ በማርያም ሥሟን ሥጠ | መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ💒

​​✟✞✟አላፍርም እኔ በማርያም✟✞✟

አላፍርም እኔ በማርያም
አላፍርም እኔ በማርያም
ሥሟን ሥጠራት እጽናናለሁ
የሐዘኔ መርሻ ብያታለሁ/፪/

/አዝማች/

ሥሟን ስጠራት በሐዘኔ ጊዜ
አጽናንታኛለች ይዞኝ ትካዜ
የመከራ ቀን የጭንቀት ደራሽ
እንደ አንቺ የለም እመቤቴ ነሽ
ማርያም ማርያም በሉ ምዕመናን ሁሉ
ማርያ ማርያምብለን እንድናለን

/አዝማች/

አደጋ ጣዮች ደርሰው ድንገት
ሥም አጠራሬን ሁሉም ጠልተውት
መታወቂያዬ አንቺ ነሽና
ሥዕልሽን ሲያዩ ጠፉ እንደ ገና
ማርያም ማርያም በሉ ምዕመናን ሁሉ
ማርያ ማርያም ብለን እንድናለን

/አዝማች/

የአሰብሁት ሁሉ በጅምር ቀርቶ
አንጋጥጣለሁ ዘመኑ በዝቶ
ፍጻሜን እንዳይ ድንግል እርጅኝ
ደጅሽ ወድቄ ተማጸንሁኝ
ማርያም ማርያም በሉ ምዕመናን ሁሉ
ማርያም ማርያም ብለን እንድናለን

/አዝማች/

አደጋ ጣዮች ደርሰው ድንገት
ሥም አጠራሬን ሁሉም ጠልተውት
መታወቂያዬ አንቺ ነሽና
ሥዕልሽን ሲያዩ ጠፉ እንደ ገና
ማርያም ማርያም በሉ ምዕመናን ሁሉ
ማርያም ማርያም ብለን እንድናለን።


በማርያም ሼር ሊንክ አድርጉ

t.me/menfesawigetem