2024-09-15 08:22:03
እዮሃ አበባዬ.............መስከረም ጠባዬ/2/
መስከረም ሲጠባ..... ተክሎ ደመራ
ህዝብ ኢትዮጵያን.......እዩት ችቦውን ሲያበራ
በታላቁ ብርሐን በመስቀል ደመራ/2/
በኃጢአት ጨለማ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ተውጠን ሳለን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የክርስቶስ መስቀል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ብርሐን ሆነልን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ትምህርተ መስቀል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ሆኖን ለመን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
በቃሉ ለምንድን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የእግዚአብሔር ኃይል ነው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
መስቀል ባንዲራችን
የነጻነት አረማችን/2/
በኢየሩሳሌም አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
አይሁድ አብረው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ያዳናቸውን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
አናውቅም ብለው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የድሉን መስቀል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ከመሬት ቀብረው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
መስሏቸው ነበር አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ውጦ ያሚያስቀረው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
በቀራንዮ ጎልጎታ
ጠላታችን ድል ተመታ/2/
ንግሥቲቷ እሌኒ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
በጣም የታደለች አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ደመራን አቁማ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ፍለጋ ጀመረች አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
መስቀለ ክርስቶስ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ወዴት ነው እያለች አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
በጣን ጢስ ተመርታ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
መስቀሉን አገኘች አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
በመስቀል መከታ
ቆስጠንጢኖስ ድል ተመታ/2/
ነገር ግን መስቀል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ተቀብሮ አልቀረም አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ተራራ አፍርሶ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ጠላት አሳፈረ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
መስቀል ሲወጣ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ታላቅ ሁካታ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ድውይ ሲፈወስ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
አንካሳው ዳነ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ሙታን ተነሱ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ይመስገን ጌታ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ብርሐን ወጣ ከመስቀሉ
ክርስቲያኖች እልል በሉ/2/
መስቀል መከታ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ይሁን ጋሻችን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
እንዳይደፈር አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ዳር ድንበራችን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ኢትዮጵያ ኑሪ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
በእምነት ፀንተሽ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ጌታ በመስቀል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የባረከሽ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
መስቀሉ አበራ
እንደ ፀሀይ ጮራ/2/
መስቀሉን አምነን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ተሳልመነዋል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ከክብሩ ዙፋን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
በእርሱ ባርኮናል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
እንሰግድለታለን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የፀጋ ስግደት አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
በእርሱ ላይ ስላለ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ሃይለ መለኮት አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
መስቀል የእኛ ጋሻ
የዲያብሎስ ድል መንሻ/2/
የኢትዮጵያን መኩሪያ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ኑ ተመልከቱልን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የመስቀሉን ብርሀን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ነፀብራቁን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
እፀ መስቀሉ ነው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የእኛ መከታችን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የተሰጠን ለእኛ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ምልክታችን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
በመስቀል እንመካለን
እንድንበታለን/2/
የዳዊት ልጅ ያዕቆብ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የሀገራችን ኩራት አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የኢትዮጵያ ንጉሥ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ጌታን የሚፈራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
መስቀል ተሸክሞ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ሀገሪቱን ሲዞር አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ድካሙን ሳይፈራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
መስቀል ተሸክሞ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ብርሐን እያበራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የመስቀሉ ፍቅር
በእኛ ላይ ይደር/2/
መናገሻ እንጦጦ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የረር አምባ አመራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ሲፈልግ ሰንብቶ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የመስቀል ተራራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ጊሸን ላይ አገኘ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የአምባሰል ተራራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ግማደ መስቀሉ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
አርፏል ከዚያ ስፍራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
መስቀል መስቀላችን
የክርስቲያን ሃይላችን /2/
የመስቀል ለታ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የደመራው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ኢትዮጵያውያን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ተደስተው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
በሀገር ልብሳቸው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
አምረው ደምቀው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
በአደባባዩ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ተሰብስበው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
ይዘምራሉ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
መስቀል ብለው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
የመስቀሉ ደመራ
በኢትዮጵያ ሲያበራ/2/
1.6K views Abreham , 05:22