Get Mystery Box with random crypto!

*የሰንበትን ቀን ትቀድሳት ዘንድ አስብ* *ይህች ታላቅ ትዕዛዝ ከ፲ቱ ትዕዛዝ አንዷ ናት። አ | መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ💒

*የሰንበትን ቀን ትቀድሳት ዘንድ አስብ*

*ይህች ታላቅ ትዕዛዝ ከ፲ቱ ትዕዛዝ አንዷ ናት። አትስረቅ፣ አትግደል፣ አታመንዝር ከሚሉት ሕግጋት እኩል ናት። እናስተውል።*

*መድኃኒታችን ሰው የሆነባት ሰንበተ ክርስቲያን: ዕለተ እሁድ ብርሃን ናት:: ይህች ሰንበት ጌታችን ከሙታን ተለይቶ ተነሳባት:: መንፈስ ቅዱስም በጽርሐ ጽዮን ወረደባት፣ በህያዋን እና በሙታን ለመፍረድም አምላካችን ዳግም የሚመጣባት ታላቅ ዕለት ናት እናም እባክህን አክብራት: ዛሬ በሰንበት የት ነህ? ዛሬ በሰንበት የት ነሽ? የት ነን?*

*ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት በሦስት ቀን አነሳዋለሁ እንዳለ ቅድስት ቤተክርስቲያን የታነጸችበት ዕለተ እሁድ ብርሃን ናት::*

*ድርሳነ መድኃኔዓለም*

*ከቀናት ሁሉ ክርስቶስ መርጦ የተወለደባት፣ የተጠመቀባት፣ ለሰው ልጅ ድህነትን፣ የሰጠባት ትንሣኤውንም የገለጠባት ይህቺ እሁድ ሰንበተ ክርስቲያን ናት::*

*ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ሰንበት ነው፤ አንተ፥ ወንድ ልጅህም፥ ሴት ልጅህም፥ ሎሌህም፥ ገረድህም፥ ከብትህም፥ በደጆችህም ውስጥ ያለ እንግዳ በእርሱ ምንም ሥራ አትሥሩ፤*

*እግዚአብሔር በስድስት ቀን ሰማይንና ምድርን፥ ባሕርንም፥ ያለባቸውንም ሁሉ ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን ዐርፎአልና፤ ስለዚህ እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ባርኮታል ቀድሶታልም* ። ዘጸአት 20:10

*እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና። በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ። ያገለግሉት ዘንድ የእግዚአብሔርንም ስም ይወድዱ ዘንድ ባሪያዎቹም ይሆኑ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር የሚጠጉትንም መጻተኞች፥ እንዳያረክሱት ሰንበትን የሚጠብቁትን ቃል ኪዳኔንም የሚይዙትን ሁሉ፥ ወደ ተቀደሰ ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፥ በጸሎቴም ቤት ደስ አሰኛቸዋለሁ፤*
ትንቢተ ኢሳ 56:4-7

*ወንድሞቼና እህቶቼ ስለዚህም በፍጹም ሰንበትን ተኝታችሁ አታሳልፉ:: ተነሱ፣ ወደ ደጀሰላሙ ድረሱ፣ ጸልዩ፣ አስቀድሱ:: ጸበሉን ጠጡ፣ ጸበል ጸዲቁን ቅመሱ፣ የታመመ የታሰረ የተቸገረ ጠይቁ።*

*በታላቂቷ ሰንበት በማለዳ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገስግሱ፣ መስቀሉን ተሳለሙ:: ግድግዳውን መሬቱን ሁሉን ደባብሱ:: ከክርስቲያን ወንድም እህቶቻችሁ ጋር  በመንፈሳዊ ፍቅር ትከሻ ለትከሻ ተሳሳሙ:: ደጉ እግዚአብሔር አባታችሁ ይጠብቃችኋል:: ያድናችኋል:: ሰላሙን ይሰጣችኋል::በዚህች የከበረች ሰንበት ማለዳ የት ነበርን?????????*

*የሰማዕቷ ድስት አርሴማ አማላጅነት የሰንበት ጸጋ እና ረድኤት በያለንበት ይድረስልን።*

ብሩህ  ሰንበት


@menfesawigetem