Get Mystery Box with random crypto!

ተሰበበረ ሰንሰለቱ ተሰባበረ ሰንሰለቱ መናወጥ ሆነ ወይን ቤቱ | መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ💒

ተሰበበረ ሰንሰለቱ

ተሰባበረ ሰንሰለቱ
መናወጥ ሆነ ወይን ቤቱ
የጌታ ማዳን ተገለጠ
እስረኛው ጴጥሮስ አመለጠ

አዝ......

ደስ ይበላችሁ እናንተ ሐዋርያት
ወንድማችሁ ጴጥሮስ ተፈታ ከእስር ቤት
የምስራች ወንጌል ስበኩ ተግታቹ
ሞትን አሸናፊ አለ ከጎናችሁ

አዝ....

ሁሩ ወመሀሩ ተብላቹሃልና
እንዳትዘናጉ በአለም ፈተና
የመከራ ማህበል ወጀቡን ስታዮ
ትግስቱን ይስጣችሁ ለበጎነው በሉ

ሁሉም ነገር ለበጎ ነው
መከራም ቢሆን ለበጎ ነው

አዝ.....

ከኛ ጋር ያለው ከእነርሱ ይበልጣል
እስር ቤት ተጥለን መቶ አፀናንቶናል
በብርሃን መስቀሉ ጎኔን ጎሽሞኝ
ወደ ፊት ሂድ አለኝ ከእንቅልፌ ቀስቅሶኝ

አዝ.....

ለሰው ከመታዘዝ ለእግዚያብሔር ይሻላል
ለህሊና መኖር ከሁሉም ይበልጣል
እስር ሰንሰለቱን ዱላውን ሳንፈራ
እንመሰክራለን የእውነቱን ስራ

አዝ....

አፅራረ ክርስቶስ እጁን ቢጭንብኝ
ወደ ሃላ አንሄድም መስቀሉን ጨብጠን
ከሞት ቦሃላ ህይወት እንዳለ እናውቃለን
እውነት ለመመስከር እንፈጥናለን

አዝ....

ሁሉም የእርሱ እንደሆነ እኛም የእርሱ ነን
ምስጋናን ለማቅረብ እንተጋለን
ምድር ተናወጠች በዝማሬ ዜማ
ሰንሰለቱ ወደቀ መዝሙሩ ሲሰማ

አዝ....

አትደንግጪ ያንኳካው ጴጥሮስ ነው
ሚካኤል ልኮት ጌታ ነው የፈታው
መዝጊያውን ክፈቺ ወዴት ትሄጃለሽ
ደስታችን ለመግለጥ ዝም በይ ትደርሻለሽ

አዝ....

የሐዋርያት ፀሎት እጅጉን ይጠቅማል
ከእስር ከሰንሰለት በእውነት ይታደጋል
በምልጃው በፀሎት ደግሞም በምስጋና
እስከ መጨረሻው እንፀናለን ገና

ተሰባበረ ሰንሰለቱ
ዘማሪት አዜብ ከበደ
ዘማሪ ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ


pls share link

@menfesawigetem