Get Mystery Box with random crypto!

ስለ እውነት የሚማሩበት ታሪክ አንድ አባት ለልጁ የሚጣፍጥ ምግብ አዘጋጀለትና በመሶብ አድርጎ አ | መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ💒

ስለ እውነት የሚማሩበት ታሪክ


አንድ አባት ለልጁ የሚጣፍጥ ምግብ አዘጋጀለትና በመሶብ አድርጎ አቀረበለት፤ ልጁም እንጀራውን እስኪጠግብ በልቶት መሶቧን ወረወራት። አባቱ "ልጄ ለምን ወረወርካት " ብሎ ጠየቀው። ልጁም "ምን ታረግልኛለች
እንጀራውንስ በላው" አለ። አባቱም "ልጄ ነገ ምናልባት እንጀራ ባይርብህም ግን ችግር ሊደርስብህ ይችላል በዛን ጊዜ ይህችን መሶብ ይዘህ ለምስክርነት ከዝህች መሶብ የበላው ሰው ነበርኩ ዛሬ ግን ቸግሮኝ ለልመና ወጣው ትላለህ መሶቧን ሳትይዝ ብትወጣ ግን ማጅራት መቺ ዱርዬ ነህ ብለው ይደበድቡሃል ልጄ ስለዚህም መሶቧ ታስፈልግሃለች" አለው። ልጁም "አይ አባቴ አታስፈልገኝም" ብሎ መለሰለት። ያን ጊዜ አባቱም "ልጄ በስሜ ትጠራ ይሆናል ነገር ግን የኔ ልጅ አይደለህም ያበላችህን ቀኜን ክደሃታልና እኔ በዝህች መሶብ
ከብሬ አንተ ግን እሷን ካድካት" አለው።
   
አባት የተባለው አብ ነው ፤ እንጀራ የተባለው ወልድ ነው፤ መሶብ የተባለችው ድንግል ማርያም ናት። 'አብ አንድ ልጁን አሳልፎ እስኪሰጥ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና' ተብሎ እንደተፃፈ! ወልድም 'የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ'
እንዳለ ስለድንግል ማርያም 'ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላታል በውስጧ ሰው ተወልዷልና' እንደተባለ። አንተም አብ በልጁ እንድትድንበት ብሰጥህ ዳንኩኝ በቃ ብለህ ለመዳንህ ምክንያት የሆነችውን ድንግልን ካድካት። ርሃብ ባያጋጥምህ እንኳን ለሌላ ችግር ትጠቅምሃለች የተባለው አንተ ሰው ነህ በምትሰራው ኃጢአት ሁሉ ስለእናትህ ብለህ ማረኝ ብትለው ጌታ ይምርሃል እናቱንም አንቺ ታስፈልግኛለሽ አማላጄ ብትላት ሁሉ ሙሉ ይሆንልሃል።
@eotcy
አንተ ግን ይህን ሁሉ አልቀበል አልክ። አባት ልጁን በስሜ ትጠራለህ ግን ልጄ አይደለህም እንዳለ አንተም ዛሬ በኢየሱስ ስም ትጠራለህ ነገር ግን የእርሱ ልጅ አይደለህም አባትህን አንተም ታውቀዋለህ ማን እንደሆነ! ያለ መሶብ እንጀራ እንዳሌለ ሁሉ ያለ ድንግል ማርያምም ክርስቶስ የለም።

በማርያም ሼር link አድርጉ

join

@menfesawigetem