2023-05-14 08:36:11
ሌሎች መንፈሳዊ ግጥሞች እና የተለያዩ የኪነጥበብ ስራዎችን ለማግኘት ከላይ ያለውን forward በመንካት ወይም ከስር ያለውን link በመንካት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@menfesawigetem
መንፈሳዊ መነባነብ
ሰአሊለነ ቅድስት
አረ አልሆንልኝ አለ መንፈሴ አልገዛም አለ
የጭንቅ አማላጂቱ አንድ ብትዪኝ
ምንአለ
ፀሎት ምህላ አቃተኝ መንፈሴ ለንሰሀ
ሸፈተ
መንፀፈዴይን ወደኩኝ ነፈሴ በሀጥያት ሸተተ።
እምቢ አለኝ ፆም ፀሎት እምቢ አለኝ
ንሰሀ
ስጋ መንፈሴ ኮብልሎ እየዋኝ ከእለም ውሀ።
አረ አንድ በይኝ እመቤቴ ወለላይቱ
ተማለጂኝ
ጨርሶ አለም ሳይነጥቀኝ ከወቅኩበት
አንሺኝ።
ነጭ ነጠላ አጣፍቼ ከቤተ መቅደስ ሰዎጣ
መፀሐፍ ቅዱስ ዘርግቼ ለስብከት
መድረክ ስዋጣ፡፡
ልበሰ ተክኖ ለብሼ ነፍቅ ገባሬ ሰናይ
ሲሆን
ጥቅስ በቃሌ ስደረድር ለዜማ ቅኔ ስቀኝ
አካሌ እዚ ሆኖ መንፈሴ እየሸፈተ
ነፍሴን በሀጥያት ገንዞ ስጋዬ ነፍሴን ጎተተ፡፡
አረ አንድ በይኝ እመብረሀን ወለላይቱ
ተማለጂኝ
ጨርሶ አለም ሳይዎስደኝ ከወደኩበት
አንሺኝ
ማለዳ ኪዳን አድርሼ ቅዳሴ ፀሎት
ጨርሼ
ከቤተክርስቲያ ወጥቼ ወደ ስጋ ገበያ ተመልሼ።
በሀጥያት ባህር ስዋኝ የግፍ ዳንኪራ
ሰረግጥ እውላለው
የልጅነት ፀጋዬን አውጥቼ ብኩርናዬን
እሸጣለው።
እዚህ መላክ መስዬ ላዬ በቅድስና በርቶ
ውጪ ከክፋት ከፍቼ ሀጥያት በፅድቅ
ተተክቶ።
በሀሜት የሰው ስጋ ስበላ በወንድሜ
ሸር ስሸርብ
ሰዋሽ ሰቀጥፍ ውዬ ስሰርቅ ሳሽሟጥጥ ስሳደብ።
ነጠላ ስለብስ ግን ወደ ቤተ
እግዚአብሔር ስገባ
ሰአሊለን ቅድስት ስል ያለ ንሰሀ እንባ።
የመውደቂያዬ ጉድጓዱ ጥልቀቱ ወሰን
ዳርቻ የለው
አዝነ ህሊናዬ ለአለም እጂ ለፅድቅ ቦታ
የለው፡፡
ማሀረነ ክርስቶስ እንዳልል ተዘከረነ ፈጣሪዬ
ሀጥያቴ በደሌ አፈነኝ በሀፍረት ነደደ ህሊናዬ።
ምን ብዬ ልጥራው ጌታዬን ተዘከረነ ብዬ
ስለኔ መገረፉን የመስቀሉን ፍቅር አቃልዬ
እንዴት ማረኝ ልበለው ስለ ስጋ ጣዕም
ተቃጥዬ።
ምንብዬ ልጥራው ጌታዬን
አይኔን ወደጠፈጠፍ ሰማይወደስላሴ መንበር
አንስቼ ማየት አቃተኝ ማረኝ ብዬ ለመናገር።
ለሰው ፃዲቅ መስዬ የሀጥያት ጎተራ ሆኛለው
እንዴት አባቴ ቀናብዬ መንበረ ፀባኦትን አያለው።
እባክሺን እናቴ ወለላይቱ ተማለጂኝ
እንደ ቃና ዘገሊላ ባዶ ማደጋዬን ሙይልኝ።
ከፊቱ እንዳላፍር ከአማኑኤ ጋር አስታርቂኝ
ለተጠማው ውሻ እንዳዘንሽ ለመፃተኛው እዘኚልኝ።
አንቺ የቱሁታን ትሁት ርሪሂተ ልብ እናቴ
ከልጅሽ ከእየሱስ አማልጂኝ እዘኚልኚ እመቤቴ
አንቺ ውዳሴሽ የነፍስ ስንቅ ስምሽ ከማር የጣፈጠ
በላዬሰብ በእልፍኝ ውሀ በምልጃሽ ከሞት ያመለጠ
አንቺ
መላእክት የሚጎበኙሽ የካህናት አለቆች ምስጋናቸው
በመወሰን የማይዎሰን እሳተ መለኮት የቻልሺው።
አንቺ
ከገነት በተሰደደ ጊዜ ለአዳም ተስፋ የሆንሺው
ዛሬም ለኔ ተስፋ ሁኚ ለነፍሴ ስለነፍሴ ተዋሺው።
እንጂ እኔማ አልቻልኩም የነፍሴ ንፅህና ጠፍቷል
ለፀሎት እንኳን ስቆም ልቤ ለሁለት ተከፈሏል።
አረ አልሆነልኚም መንፈሴ አልገዛም አለ
የጭንቅ እማላጂቱ አንድ ብትይኝ ምን አለ
እምቢ አለኝ ፆም ፀሎት እምቢ አለኝ ንሰሀ
ስጋ መንፈሴ ኮብልሎ እየዋኝ ከአለም ውሀ።
የልቤን መዎላዎል የነፍሴን ድካም አበርቺ
በአማላጅነትሽ ስር ነኝእና ከልጅሽ አስታርቂኝ አንቺ።
ለሰው አይን ባይገለፅም ሰውሬ የሰራሁት ሀጥያት
አምላክን አሳዝኖታል የምኖርበት ህይዎት።
ይሀው
የምናገረው አይሰምር የዎረወርኩት አይመታም
ስጋዬ አልተቀደሰ ገበታዬ በረከት የለውም።
እውቀት ምርምር አይዘልቀኝ ህሊናዬ ፍሬ አይቋጥር
ዝሩ ሆኖ ቀርቶብኝ የነፍስ የስጋዬ ሚስጥር።
ይሀው
የማዎራው ለሰው አይጥምም ፍቅር ከኔ ቤት ርቋል
መቆም መቀመጤ አያምር ሰው በስራዬ ይማረራል።
የሀጥያት ምንዳዬ ይሀው የሀጥያት ደሞዜ ይሀው ስቃይ ውስጤን በልቶታል
ለአንድነት የተናገርኩት ዛሬም ጉባኤ ይበትናል።
እና አዛኚቱ ታረቂኝ ከልጅሽ ከአማኑኤል አማልጂኝ
ከሰው የሸሸኩት ሀጥያት ጨርሶ በልቶ ሳይዉጠኝ
የበላዬሰብ እመቤት እባክሽን ተማለጂኝ
አንቺ ህይዎቴን ዳብሺው ነፍሴ ህይዎት እንድታገኝ
አረ አልሆነልኝም መንፈሴ አልገዛም አለ
የጭንቅ አማላጂቱ አንድ ብትይኝ ምን አለ
ፀሎት ምህላ አቃተኝ መንፈሴ ለንሰሀ ሸፈተ
መንፀፈዴይን ወደኩኝ ስጋዬ ነፍሴ ሸተተ
እምቢ አለኝ ፆም ፀሎት እምቢ አለኝ ንሰሀ
ስጋ መንፈሴ ኮብልሎ እየዋኝ ከአለም ውሀ
አረ አንድ በይኝ እመቤቴ ወለላይቱ ተማለጂኝ
ጨርሶ አለም ሳይነጥቀኝ ከዎደኩበት አንሺኝ
እባክሺን ተማለጂኝ እናቴ ኪዳነ ምህረት
ተስፋ ክብራችን አንቺ ነሽ
ሰአሊለነ ቅድስት
ሰአሊለነ ቅድስት
መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ
በማርያም በእመብረሀን ሼር ሊንክ አድርጉ
2.6K viewslog out, edited 05:36