Get Mystery Box with random crypto!

​​ የዳቢሎሷ ልጅ ምእራፍ 3 . . . . ....ቀኑ ተገባዶ መሽቶ ወደ መ | Y Ethio class

​​ የዳቢሎሷ ልጅ

ምእራፍ 3
.
.
.
.
....ቀኑ ተገባዶ መሽቶ ወደ መኝታዬ ስሔድ ግን ሀሳቤ ያዶት ወንዝ ላይ
እንደተጣበቀ ነበር …::እንቅልፌ ሁሉ የተቆራረጠ ..ለሊቱ የረዘመና
የተንቀራፈፈ ሆነብኝ…ክፋቱ ደግሞ ሰዓት ራስጌዬ አድርጌ ነው የተኛውት…
ተኝቼ ተኝቼ ስባንን 8፡16 ተኝቼ ተኝቼ ስነቃ 9፡34 ተኝቼ ተኝቼ ስባንን 10፡13
ተኝቼ ተኝቼ ወይኔ ተበላው ነጋብኝ ብዬ ስነቃ 11፡20 ከዛ በላይ መተኛት
አልቻልኩም፡፡
ተነሳው ሹክክ ብዬ ልብሴን ለበስሼ ሹክክ ብዬ ጄሪካኔንና ማዘያውን ይዤ
በቀስታ በራፉን ከፍቼ ወጣው..ይስፈራል…. ከጭለማው ጋር አይኔን
እስከማለማምድ ደቂቃዎች ወስደውብኝ ነበር….በጭራሮ ታጥሮ በጭራሮ
በር የተዘጋውን የጊቢያችንን አጥር መሸንጎሪያ አውጥቼ ከፈትኩና ወጣው…
ግን መቀጠል አልቻልኩም ልቤ ለሁለት ተሰነጠቀ..ሂጂ ጭግር የለውምም››
..አረ ተይ ሰው አግኝቶ ባይተናኮልሽ እንኳን አውሬስ ቢዘነጥልሽ…ከግቢያችን
መቻል በጩኃት ያንቧርቀው ጀመር…አንድ ሀሳብ መጣልኝ… ተመልሼ ወደ
ጊቢ ገባውና ወደ እሱ ሄድኩ …መጩሁን ተወና እግሬ ስር ሽብልል ብሎ
ተኛ..ቀስ ብዬ በሹክሹክታ ልክ እንደልብ አውቃ ጎዳኛ..<<አብረን እንሂድ
ተነሳ…>>አልኩትና መንገዴን ወደ መውጫው ቀጠልኩ ..ተከተለኝ..::
አዎ አሁን ቀለል አለኝ…ቢያንስ አሁን ይሻላል…….ወንዙ ጋር ስንደርስ ገና
ጭለማው እንደመግፈፍ እያለ ወፎቹ እየጩሁ ነበር…መቻል ከኃላዬ ከኃላ
ኩስ ኩስ እያለ ነው..በዛፎቹ ላይ ያሉት ወፎች የለሊ ዝማሬያቸውን
ያሰማሉ..እንደደረስኩ ጄሪካዬን አንከርፍፌ ለአስር የሚሆን ደቅቃ ፈዝዤ
ወዲህና ወዲያ አይኖቼን በማንከራተት የሆነ ነገር እፈልግ ነበር..
እንዴ ምንድነው የምፈልገው….ጄሪካኑን ይዤያለው…የወንዙም ውሀ በእግሬ
ላይ እያለፈ ወደ ፊት እየተመመ ነው..እና ለምን ጎንበስ ብዬ አልቀዳም ..?
ለምን በብርድ እንዘፈዘፋለው….አዎ መቻል ማንቧረቅ ጀመረ….. ግረ ገብቶኝ
አይኖቼን ሳቅሎጨልጭ ከወንዙ መሀል ብልቅ ብሎ ወጣ…
‹‹የፈጣሪ ያለህ..>> ጩኀቴን ለቀቅኩት.ደግነቱ የእኔ ጩኃት ከመቻል ጩኸት
ስለማይበልጥ ተውጦ ቀረ…
‹‹ዛሬም ደነገጥሽ?››
‹‹ምን አይነት ሰው ነህ…..?ቤትህ ወንዙ ውስጥ ነው እንዴ?››በመገረም
ጠየቅኩት
‹‹አዎ …ከፈለግሽ ነይ ልብስሽን አውልቂና ግቢ ….በዛውም ቤቴን
አሳይሻለው››
‹‹ቤትህን ባየው ደስ ይለኝ ነበር… ግን ዋና አልችልም››አልኩና ለቀቀልድ
ምላሽ ሰጠውት
‹‹የመና ልጅ ሆነሽማ ዋና አልችልም ብትይና አላምንም…ደሎ እንኳን ሰው
ከብቶቹም ዋና ይችላሉ››
‹‹ቢሆንም ይቅርብኝ ..ባይሆን ሌላ ጊዜ እልኩና ጎንበስ ብዬ ጄሪካኔን ወደ
ውኃ ውስጥ ከተትኩት…መቻልም ድምፅንአጥፍቶ በሜትሮች ርቀት መሬት
ላይ ለጥ ብሎ ሁለኔታችንን እየታዘበ ነው፡፡
‹‹እንግዲያው ቀረብሽ ››ብሎ መልሶ ወደ ውሀ ውስጥ እራሱን ደፈቀና
ሰመጠ ክእይታ ተሰወረ…የሆነ ነገሬን ይዞ የሄደ ነው የመሰለኝ…እንዳለኝ
ልብሴን አወላልቄ ወንዙ ውስጥ መግባት እና አበሬው መዋኘት በጣም
አሰኝቶኝ ነበር..ግን ፈርቼ ነው…በዚህ ሰእት እርቃኔን ወንዝ ውስጥ
ከማላውቀው ሰው ጋር…ግን ምን ችግር አለው…ባደረግኩት ኖሮ ቁጭት…
አንድን ነገር እኩል መፈለግ እና እኩል አለመፈለግ እንዴት ነው የሚቻለው
ከአሁን አሁን ከሰመጠበት ይወጣል ስል.. ስጠብቀው…ጄሪካኑ ሞላ..ጎትቼ
ከወንዙ ውስጥ አወጣውት እና ዳር ላይ አስቀመጥኩት….ጄሪካኔን ተሸክሜ
ጉዞዬን መቀጠል ነበረብኝ …ግን እግሬ ሊንቀሳቀስልኝ አልቻለም .ተመስገን
ነው ብልቅ ብሎ ወጣ….
‹‹ቸው በቃ ልሂድ››አልኩት
‹‹አረ ትንሽ..እስቲ ስምሽን ንገሪኝ?››
‹‹ምን ያደርግልሀል?››
‹‹ያው ቆንጆ ልጅን ስም ማወቅ ያጎጎል ..ለዛ ነው››
አፈርኩና አቀረቀርኩ
‹‹ንገሪኛ አለኝ…? በጀርባው ተንጋሎ በመዋኘት ወደ እኔ እየተጠጋ
‹‹በሬዱ››
‹‹አንቺ ቆንጆ ስምሽም ቆንጆ አሪፍ ነው››አለኝ
ፈራ ተባ እየልኩ ‹‹ያንተስ..?››አልኩት
‹‹የእኔን ሌላ ቀን ከእነ ትርጉሙ አነግርሻለው››
‹‹እንዴ ሌላ ቀን እንጋናኛለን እንዴ?››
‹‹ጥያቄዬ ማረጋጋጫ እንዲሰጠኝ የመፈለግ አይነት ነወ…››
የልብ አውቃ ነው‹‹እንዴ !!!ትቀልጂያለሽ እንዴ ..?እኔ እና አንቺ ጋና ብዙ ጊዜ
ይኖረናል …ብዙ ታሪክ እንጽፋለን››
‹‹የምን ጊዜ…?የምን ታሪክ..?››
‹‹የፍቅር ታሪክ ››
‹‹የፍቅር ….?ምን አይነት አይንአውጣነት ነው…አረ እኔ እንደዚህ አይነት ነገር
አላውቅም….››
እንደማታውቂ እውቃለው…. እኔም አላውቅም ….ግን አብረን
እንማረዋለን››ብሎኝ እርፍ
‹‹በል ይበቃሀል አሁን ልሂድ..ብዬ የግዴን ጄሪካኔን አንጠልጥዬ ተሸከምኩና
ፊቴን አዞርኩ››
‹‹በይ ደህና ዋይልኝ..ነገ በዚህን ሰዓት እጠብቅሻለው….
‹‹አታስበው…..ገን የእውነት እቤትህ እዚሁ ሳይሆን አይቀርም ››አልኩት
እየሄድኩ
‹‹አሳይሻለው ብዬሽ የለ..? አሳይሻለው…መቶ ሜትር ያህል ከራቅኩት ቡኃላ
ዞር ብዬ አየውት ደብዛው የለም…መልሶ ሰምጦ ይሆን..?ይሄ አፍዛዝ ውበት
ያለው ልጅ ሰይጣን ሳይሆን አይቀርም..?የወንዝ ሰይጣን…ግን እንዲህ
አይነት ጠንበል ሰይጣን ካለማ ይገርማል…ቤተ ክርስቲያን ግድግዳ ላይ
የተለጠፈው ስዕል ቅዱስ ሚካኤል እግር ተጨፍልቆ የሚታየወን አስፈሪውና
ሰይጣን በምስሌ መጣብኝና..ከዚህ ኛው ጋር አስተያይቼ በራሴ
አፈርኩ..በስመአብ ይቅር ይበለኝ…

ይቀጥላል....10 comment እጠብቃለሁ