Get Mystery Box with random crypto!

የዳቢሎሷ ልጅ ምእራፍ . ... አሁን ወደራሴ ልመልሳችሁ፡፡ምክንያቱም እናቴ የ | Y Ethio class

የዳቢሎሷ ልጅ

ምእራፍ

.
...
አሁን ወደራሴ ልመልሳችሁ፡፡ምክንያቱም እናቴ የጀመረችውን ታሪክ
ለመጨረስ እንዲህ በቀላሉ የምትችል አይነት አልመሰለኝም፡፡ይታያችሁ
እስከአሁን የአባቴን ከንፈር እንደሳመችው ወይም እንደሳማት እንኳን
አልገለፀችላችሁም፡፡እንግዲህ በዚህ አካሄዶ የእኔ መወለድ ጋር ለመድረስ
ስንት ምዕራፎችን መጠበቅ እንዳለባችሁ መገመት አይሳናችሁም ብዬ
አስባለው…እኔ ደግሞ ያን ያህል መጠበቅ አልችልም፡፡ባይሆን በመሀል
እለቅላትና የጀመረችውን ታሪክ ትጭስላላችሆለች፡፡
ለዛሬ ግን ራሴ ላውራችሁ..ስለዛሬ ..አሁን ስላለውበት ሁኔታ…
አሁን ያለውት አዲስ አበባ ነው ሲ ኤም ሲ አካባቢ ነው፡፡በነገራችን ላይ አዲስ
አበባ ብቅ ስል ማርፍበት የራሴ የሆነ ቤት አለኝ፡፡ 1ሺ ካ.ሬ ሜትር ግቢ ላይ
ጥጉን ይዞ በታነፀ ባለሶስት ክፍል መጠነኛ ቢላ ቤት ውስጥ ነው የምኖረው፡፡
….ከቤቱ ይልቅ በግቢ ውስጥ ያሉ ዛፎች ዕጻዋቶች እና ፍራፍሬዎች ይበልጥ
ያስደምማሉ፡፡ በግቢዬ ውስጥ ከ140 በላይ የዕፅዋት አይነቶች ይገኛሉ፡፡
ከነዚህ ውስጥ 83ቱን ከተለያዩ አህጉራት በዞርኩበት ወቅት ቀልቤን ስበውት
አወይም አስደምመውኝ አምጥቼ የተከልኮቸው ናቸው፡፡እርግጥ
አልዋሻችሁም አምጥቼ የተከልኮቸው ከዚህ አሁን ከጠቀስኩላችሁ ቁጥር
በሶስት እጥፍ ከፍ ያለ ነበር..ከአዲስ አበባ የአየር ፀባይ ጋር ተላምደው ግን
መጽደቅ የቻሉት እነዚህ ብቻ ናቸው፡፡
ግቢዬ ውስጥ ያሉ ዕጽዋቶች ሁሉ አስደማሚነታቸው ለአይን መስብ
ከመሆናቸውእና ንጽ አየር ሚያመርቱ ፋብሪካዎች ስለሆኑ ብቻ አይደለም
እዚህ ግቢ የመተከል ተተክሎም የመብቀል እድል ያገኙት…እያንዳንዱ የተለየ
ሚስጥር እና ጥበብ የሚገለጽባቸው የእግዚያብሄርን ሚስጥራዊ ሹክሹክታ
በቅጠሎቻቸው እና በስሮቻቸው ስለሚተነፍሱ ነው…::መድሀኑት ናቸው…
ታአምራትን የሚሰራባቸው ናቸው..ብዙ ብዙ ነገር…በየዛፎች ቅርንጫፍች ላይ
ቁጥራቸውን የማላውቃቸው የወፍ ጎጆዎች ሞልተውባቸዋል፡፡ሶስት ጉሬዛ እና
አራት ዝንጀሮዎችም አሉኝ ..ሁሉንም ያመጣዋቸው ከአገሬ ጫካ ነው… ከደሎ
መና፡፡
አብረውኝ የሚኖሩ አንድ የስልሳ ሁለት አመት አዛውንት ሰውዬ አሉ፡፡ጋሽ
ተክለወልድ ይማም ይባላሉ፡፡ይሄንን ጊቢ እንዲህ ያሳመርኩትም
የማስተዳድረውም ከእሳቸው ጋር ነው፡፡
እኔ ያው አብዝቼ ከአንድ የምድር ጫፍ ወደሌላው መስፈንጠር የዘወትር
ድርጊቴ ስለሆነ በሌለውበት ጊዜ እሳቸው ናቸው ሙሉ ሀላፊነቱን
የሚወስዱልኝ፡፡ዘበኛ ናቸው ወይም አትክልተኛ ናቸው እያልኩ አይደለም፡፡
ከዕጽዋቶች ጋር በፍቅር የወደቁ ከሀለማያ ዩኒቨርሲቲ ለ32 ዓመት ያስተማሩና
በቅርቡ ጡረታ የወጡ የዕጽዋት ተመራማሪ ፕሮፌሰር ናቸው፡፡ስለእሳቸው
ጠለቅ ያለ መረጃ ሌላ ጌዜ ነግራችሆለው ፡፡
በነገራችን ላይ ዋናውን ያለኝን ነገር አልነገርኮችሁም፡፡ንስር አሞራ አለኝ ፡፡
ንስር አሞራ ስላችሁ ሌላ ስለእሱ ለእናንተ የማስረዳበት መንገድ ስለሌለ ነው፡፡
እያንዳንዱ ሰው ልጅ እንዲጠብቀው እንዲንከባከበው እና ከክፉ ነገር
እንዲከልለው ከፈጣሪው የተመደበለት ጠባቂ መልዐክ አለው ብዬ
አምናለው፡፡ግን እነዚህ ጠባቂ መላዕክቶች አካል አልባ መንፈስ ናቸው ፡፡
አይታዩም፡፡መታየት ብቻ ሳይሆን አብዛኛው ሰውም ጠባቂ መልአኩን በትከሻው
ላይ ተሸክሞ እንደሚዞር አያውቅም… አያምንምም፡፡
ስለዚህ አይገለገልባቸውም …አያዳምጣቸውም፡፡ሰው በጨለማ ውስጥ
ሲጎዝ ማጅራት መቺ ከኃላው ካለ ምንም አይነት እንቅስቃሴ ሳይሰማ ትከሻዬን
ከበደኝ ይላል፡፡ያ ምን ማለት ይመስላችሆል…. እሱ ያልተመለከተውን
በጭለማ ውስጥ የተሸሸገውን አጥቂውን ጠባቂ መልአኩ አይቶት ሹክ
ብሎታል ማለት ነው፡፡እንግዲህ ያ ሰው ብልህ ከሆነ ማድረግ ያለበት
መልዕክቱን አምኖ ተፈትልኮ በመሮጥ ማምለጥ ወይም ጥቃቱን ለመመከት
እራሱን ማዘጋጀት ነው፡፡አይ ዝም ብሎ ተራ ፍራቻ ነው ብሎ የደረሰውን
መልዕክት ችላ ብሎ በእንዝላልነቱ ከገፋበት ግን ማጃራቱን ተመቶ
ይዘረራልም..ይዘረፋልም ማለት ነው፡፡
እና ለእኔ ይሄ ንስር አሞራ ጠባቂ መላዕኬ በሉት፡፡ከእናንተ ከተራ ሰዎች
በጣም የላቀ ማንነት እና ብቃት አለኝ የምላችሁ አንድም ለዚህ ነው፡፡በአካል
አብሮኝ የሚንቀሳቀስ የሚያወራኝ የማወራው ጠባቂ መልአክ ስላለኝ፡፡
የፈለግኩበት የአለም ጥግ አንጠልጥሎ የሚወስደኝ..ከሚንቀለቀል እቶን
እሳት ውስጥ ብገባ እንኳን አንጠልጥሎ በማውጣት ሀይቅ ውስጥ ጨምሮ
የሚያቀዘቅዘኝ፡፡
ካለሀሪ በረሀ ላይ ወስዶ በጥም ጉሮሮዬ ከደረቀ ከመንቁሩ ወይን አመንጭቶ
የሚያጠጣኝ…..የሲ.አይ .ኤን የስለላ መረብ በጣጥሶ የዋይት ሀውስ ራት
ግብዝ ላይ አስገብቶ የሚጥለኝ፡፡ሱፐር ሂዩማን እንድሆን ሱፐር ሆኖ ሱፐር
የሚያደርገኝ መልዐኬ ነው፡፡
በንስር አሞራ አካል ያለው የመላዕክት ነፍስ፡፡ንሰሩ ያየውን አንደማይ እና
ያሰበውን እንዳመስብ አውቃለው፡፡ልክ በአንድ ዲኮደር እንደሚሰራ ሁለት
ቴሌቪዝን በሉን….እኔ ቤቴ ቁጭ ብዬ እሱ አየሩን ሰንጥቆ በሚበርበት
የምድር ጥግ ሁሉ እያየ ያለውን ነገር ጥርት ባለምስል በአዕምሮዬ አያለው…
የንስርን አይን ደግሞ የምታውቁት ነው..እያንዳንዱ ንስውር ቅንጣት በቀላሉ
በአይኑ ሌንስ ይቀልባታል፡፡ይሄ ገለጻዬ ለብዙዎቻችሁ ግራ ሊያጋባ ይችላል፡፡
ይሄ መልአክ ነው ሰይጣን ልትሉ ትችላላችሁ፡፡መልአክ ከሆነ ለምን በእርግብ
አካል ውስጥ አላደረም ወይንም እንደተለመደው ለምን የበግ ስጋና ቆዳ
አለበሰም፡፡እሱን አላውቅም ነው መልሴ…. ደግሞም ግድም አይሰጠኝም፡፡
ዋናው በእርግጠኝነት የማውቀው ነገር የእኔ እኔነት እና የንስሩ ነፍስ የተሳሰረ
መሆኑን ነው፡፡
የኖረውን ያህል ኖሬ በሚሞትበት ቀን የምሞት እንደሆነም ይሰማኛል፡፡
ወይንም የእሱ ነፍስ ከንስር አካሉ ውስጥ ተንጠፍጥበፎ በሚወጣበት ቅጽበት
የእኔም ነፍስ ከዚህ የሰው ሰውነት ወይም አካል ውስጥ ተንጠፍጥፎ
በመውጣት ከእሱ ነፍስ ጋር በመተቃቀፍ ወደሚሄድበት ሚስጥራዊ ቦታ
አብሮት እንደሚነጉድ አውቃለው…የመዳረሻችን ፍጻሜውም የአምላክ እቅፍ
እንደሆነ ይሰማኛል ፡፡
አሁን ባለንበት ቦታ ሁለታችን ደስተኞች ነን ፡፡በዚህች ምድር ሚስጥር
እየተደመምንም ነው፡፡እርግጥ እኔ እና ንስሬ ከዚህች ምድርም አልፈን
ሌሎችንም ፕላኔቶች ለመቃኘት ሞክረናል፡፡ግን ከሁሉም ከሁሉም እንደምድር
የተዳለ እና በእግዜያብሄር ጸጋ የረሰረሰ ስፍራ አልገጠመንም፡፡
የእውነቱን ስነግራችሁ ምድር በጣም እድለኛዋ ፈለክ ነች..በህይወት
የታጨቀች..የእግዚያብሄር የመዳፍ ስራ መገለጫ ወርክ ሾፑ ነች ማለት
ይቻላል…፡፡ይሄ የሆነው ዋናው ምክንያት በፀሀይ ውስጥ የያዘችው ስፍራ
ነው… ለፀሀይ በጣም ቅርብ የሆኑ ስነ-ፈለኮች በጣም ሞቃትና በጨረር
የተጨቁ ናቸው..በዚህ ምክንያት ህይወት ሊበቅልባቸው ምቹ አይደሉም፡፡
ከፀሀይ በጣም የራቁ ፈለኮች ደግሞ በቂ ብርሀን ከፀሀይ ስለማይደርሳቸው
በጣም ቀዝቃዛ ይሆናሉ..በዚህም የተነሳ ህይወት ያለውን ነገር ለማኖር
ምቹዎች አይደሉም.. በዚህ ግን መሬት የታደለች ነች፡፡ በጣምም ያራቀች
እጅግም ያልቀረበች አራታኛውን ወይም መሀከለኛውን ስፍራ የያዘች ነች…
ስለዚህ የተመጠነ ብርሀን እና ሙቀት ነው የሚደርሳት ..በዛ ምክንያት በስነ-
ህይወት የተንበሸበሸች ነች…፡፡
ማርስ ህይወት አላት የላትም የሚባለው ክርክር ሁል ግዜ የሚነሳውና
የሚያጨቃጭቀው አንድም ከመሬት ቀጥሎ