Get Mystery Box with random crypto!

​​​​ ♂የሰፈሬ ልጅ እውነተኛየፍቅርታሪክ | Y Ethio class

​​​​ ♂የሰፈሬ ልጅ

እውነተኛየፍቅርታሪክ

የመጨረሻው ክፍል

... ጉዴን ይነግረኝ ጀመር ቢኒ ወደ ጢስ አባይ አጎቴ ጋ እሄዳለው ያለኝ አውቆ እንደሆነ እና
እናቴ ዘንድ ወደ አ/አ እንደ ሄደ እናቴ ደማነስ ስላለባት በጣም ታማ ስለነበረ እሷ ሊያያት እንደ ሄደ ነገረኝ ድብስ ብስ አድርጎ ተናግሮ ማለፍ ፈለገ እኔም በጣም ገረመኝ አንድ ጥያቄ የፈጠረብኝ ነገር አለ አልኩት ቢኒ ይሄን ታክል ለእናቴ መስዋትነትን የከፈለ ለም
ንድን ነው አልኩት ያን አላውቅም አለኝ ምን አልባት ሰለሚወድሽ ይሆናል አለኝ በዚህ ዘመን ምን አይነት ፍቅር ነው"" ይሄን ታክል መስዋትነት የሚያስከፍል አልኩኝ አቤል እውነቱን ልንገርህ አደለ ላለመናገር ስለፈለክ እንጂ የሆነ ሚስጥር እንዳለ ይገባኛል አልኩት እንደዛ ለምን ታስብያለሽ እያለ ብዙ ቀባጠረብኝ እንደ ማይነግረኝ ሳውቅ አመሰግናለሁ በቃ ቻወ አልኩት ለተወሰነ ሰከንድ ዝም አለኝ

ማውቅ የለለብሽን ባታውቂ ምን ይቀርብሻል አለኝ ሚጠቅመኝን አኔነኝ ማውቅ አልኩትኝ አሺ በቃ ሰረኬን ጠይቂያት አለኝ ሰርኬ ማለት ሰራተኛችን ናት አሁን የባሰ ደነገጥኩ እንነዚህ ሰዋች ቢኒ እንዴት አድርጎ ቢቆልፋቸው ነው ይሄን ታክል ለመናገር የከበዳቸው አልኩኝ እሺ ብዬ ተሰናብቼው ተለያየን ሰራተኛችን በሌላ ቀን ማታ ላይ ብዙ ስናወራ ቆየንና ከብዙ ጭቅ ጭቅና ንትርክ በኃላ ቢኒ ይሄን ሁሉ ሊያደርግ የቻለው የቢኒ እናት ለእናትሽና ለአባትሽ መለያየት ዋና ምክንያት ናት አለችኝ ደነገጥኩኝ የቢኒ እናት በጣም ክፉና ወረኛ ሰለነበረች ለእናትሽ ሰለአባትሽ መጥፎ ነገር እየተናገረች እንዲፋቱ ያደረገች እሷ ናት አለች ከዚያን በኃላ አባትሽ ታሞ ስለ ነበረ ብዙም ሳይቆይ እንደ ሞተ እና እናቴም የአባቴን መሞት ስትሰማ ከዛን ቀን ወዲህ በሽተኛ እንደሆነች ብዙ ስቃይ እንዳሳለፈች በሰአቱ ገና ህፃን እንደ ሆንኩ ነገረችኝ ቢኒ ይሄን ሁሉ ሰለ ሚያውቅ እናቱ ጋር ተጣልቶ አባቱ ጋር እንደ ሚኖር እና እናቴ የሞት አፋፍ ላይ ሁና ታማ እንኩላሊቱን እንደ ሰጣት በተለያየ ግዜ ደግሞ ደማነስ ስላለባት ደሙን እንደ ሰጣት ነገረችኝ ይሄን ሁሉ ያደረገው እናቱ የበደለቻትን እሱ ሊክሳት እንደ ሆነ እኔንም ሰለሚወደኝ ይሄን ሁሉ እንዳደረገ ስትነግረኝ የሰማሁትን መቀበል አቃተኝ በእንባ ታጠብቁ ቢኒ የልጅ አዋቂ ነው እድሜውና አስተሳሰቡ አይገናኝም ብህይወት እስካለሁ ድረስ ቢኒን እንደ ምጠብቀው ለራሴ ቃል ገባሁ።

ከብዙ ልፋት በኃላ እኔም በጥሩ ውጤት ተመረኩኝ ወድሜ በጣም ደስ አለሁ ህይወት ቀጠለች ስለ ቢኒ ሳልስማ አመታት አለፈኝ እሁድ ቀንን አወደዋለሁ ጉዋደኞቼ ጋር ስንዝናና ውለን ወደ ቤት መጣሁ
ሰራተኛችን ሳያት ተኝታለች እኔም ልረፍ ብዬ ወደ ሩሜ ስሄድ
ለስለስ ያለ ሙዚቃ ተሰማኝ ወደ ክላሴ የምሄድበት ኮሪደር እንደ ጨፌ የተጎዘጎዘ ቀይ ፅገሬዳ አየሁ የልቤ ምት ሲጨምር ይታወቀኛል ቀስ ብዬ በሩን ከፈትኩት በህይወቴ ብዙ ሚያምሩ ክለሶችን አይቻለሁ እንደ ዛሬው ግን የሚያምር ክላስ አይቼ አላውቅም ወደ ወስጥ ገበሁ ሳለሰስበው ከኃላዬ አይኔን ከደነኝ ድምፁን ጎርነን አደርጎ እኔ ማነኝ አለ ቢኒ ነው ከደስታዬ ብዛት የተነሳ ጨውኩኝ ተጠመጠምኩበት
ብዙ ግዜ አልቅሻለሁ እንደ አሁን ግን የደስታ እንባ አላለቀስኩም
በቃ ቢኒ ማለት ለእኔ ወንሜ እህቴ እናቴ አባቴ ጓደኛዬ ፍቅረኛዬ ነው በህይወቴ አልሜው የማለውቀውን ነገር አደረገለኝ የእናቴን ቀለበት አሰረልኝ ከዚህ በላይ ፍቅር የት አለ ለቢኒ አረገዝኩለት ህይወት ትቀጥላለች ። አንድ የምወደው የመጽሀፍ ቅዱስ ቃል አለ

#በለሱንየጠበቀፍሬውንይበላልጌታውንየጠበቀይከብራል

እናንተም ከእኔ ህይወት ብዙ እንደ ተማራቹ ተስፋ አደርጋለሁ!!

//ተፈፀመ//


ምስጋና
ታሪኩን በመከታተል አስተያየታችሁን ላደረሳችሁኝ በሙሉ!

በታሪኩ ላይ ያላችሁን አስተያየት ከታች አስተያየት comment የሚለውን በመንካት ያድርሱን፡፡

. ꧁༺༒༻꧂
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share ◉●••

┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄

LℐᏦℰ Ꭿℕⅅ ЅℋᎯℛ★彡