Get Mystery Box with random crypto!

የዲያቢሎሷ ልጅ ምእራፍ . . . . ሚሥጥር ማነፍነፍ፤የሠውን ገበና መበርበር፤የወዳጆች | Y Ethio class

የዲያቢሎሷ ልጅ

ምእራፍ


.
.
.
.
ሚሥጥር ማነፍነፍ፤የሠውን ገበና መበርበር፤የወዳጆችን
ሹክሹክታ መጥለፍ ዋና ባህሪዬ ነው።ከምግብ እኩል
ሚሥጥር ነው የሚያኖረኝ።በተለይ በትልልቅ ነጋዴዎች
መካከል የሚደረግ ሚስጥራዊ ድርድር...በፓለቲከኞች
መካከል ከመጋረጃ ጀርባ የሚካሄድ ድርድር ማነፍነፍ
የተፈጠርኩበት ዋና የህይወቴ አላማ ነው።
ይህ አብሮኝ የተወለደ በተፈጥሮ የተሠጠኝ ችሎታ ቢሆንም
እኔ ደግሞ በተለያዩ መንገዶች አሣድጌዋለሁ አዳብሬዋለሁ...
ለምሣሌ በወንጀልና ሥለላ ላይ የተጻፉ መጽሀፎችን ማንበብ
ፊልሞችን መመልከት...በየእለቱ የምከውናቸው ተግባራት
ሢሆኑ ለዚህ እንዲረዳኝ በቂ የሆነ ወታደራዊ
ሥልጠና፤የሥለላ ጥበብ እና ጠለቅ ያለ የኮምፒውተር
እውቀትን ገብይቻለሁ...አሁን 32 አመቴ ላይ ነኝ።ይሄንን
በእቅዴ አሥገብቼ ዝግጅት ማድረግ የጀመርኩት ከ17 አመቴ
ጀምሮ ነው።
እሥቲ ፈታ አድርጌ ላሥረዳችሁ ልጅ ሆኜ ጀምሮ አንድ ሠው
ሢያወራ እኔ ማዳምጠው ሠውዬው በቃላት ከሽኖ
የሚያሥተላልፈውን መልእክት ሣይሆን በሚናገራቸው
ቃላቶች አድበሥብሶ ወደ ውሥጡ ያሥቀራቸውን እና
የደበቃቸውን ቃላቶች ተሠብሥበውና ተገጣጥመው አንድ
ላይ በመጣመር የሚያሥተላልፉትን መልእክት ነው።እኔ
ማዳምጠው ሥሜቱን ነው..የፊቱ ቋጠር ፈታ ላይ
የሚነበበውን መልእክት ነው..በዛ ደግሞ ከማንም ጋር በነፍሴ
እንኳን ቢሆን አሥይዤ መወዳደር እችላለሁ...ሊነክሠኝ
የመጣንና ሊሥመኝ የመጣን ሠው ገና በኪሎ ሜትሮች ርቀት
ነው መለየት የምችለው...በተለይ ማወቅ ፈልጌ ትኩረቴን
ሠብሥቤ ትንሽ ካውጠነጠንኩ በቃ የሆነ መንፈሥ አየሩን
ሠንጥቆ በመምጣት ሚሥጥሩን በጆሮዬ ሹክ ይለኛል...
ለነገሩ ሁሉ ነገሬ ከሠው የማይገጥም እና የተለየ የሆነው ገና
ከውልደቴ ጀምሮ ነው።
የተወለድኩት እንደማንም የሠው ልጅ በዘጠኝ ወሬ
አይደለም..አንድ አመት ከሥድሥት ወር በእናቴ ማህጸን
ውሥጥ ዘና ብዬ ኖሬያለሁ...ምን አልባት በሠው ልጅ
የህይወት ታሪክ በእናቱ ማህጸን ከበቂ በላይ ለሆነ ጊዜ
በመንደላቀቅና በምቾት በመኖር ሪከርዱ በእጄ ሣይሆን
አይቀርም..እርግጥ ብዙዎቹ ይሄንን ታሪክ ሢሠሙ
ባለማመንና በመጠራጠር ክርክር ውሥጥ ይገባሉ<...እናትሽ
አንቺን የፀነሠችበትን ቀን ተሣሥታ ነው>የአብዛሃኞቹ መላ
ምት ነው..ግን ይሄ እንዳልሆነ ከመጀመሪያ ሣምንት የጽንሠቷ
ጊዜ አንሥቶ እሥክትገላገል ድረሥ የሀኪም ክትትል ውሥጥ
ሥለነበረች ትርክቴ በሳይንሥ መረጃ የተደገፈ ነው..ይሄም
በተወለድኩበት ሣምንት በኢትዮጵያ ሬድዮ የቀትር ዜና ላይ
<<በባሌ ክፍለሀገር በደሎ መና ከተማ ኑዋሪ የሆነችው በሬዱ
ዲንቃ የምትባል ወጣት ሤት በአንድ አመት ከሥድሥት ወሯ
ጤነኛ የሆነች ሤት ልጅ መገላገሏን ከከተማው ጤና ጣቢያ
በደረሠን ዜና ማወቅ ተችሏል።....>>የሚል ዜና ተነግሮ
ሥለነበር ከመወለዴ የከተማዋ ዝነኛ እና ታዋቂ ሆኛለሁ።
አይዟችሁ ገና አትገረሙ።እራሤን ችዬ መቀመጥ የጀመርኩት
በሶስት ወሬ ነው...በሥድሥተኛ ወሬ መራመድ ጀመርኩ
በአንድ አመቴ እቤታችን ውሥጥ በእኩል ደረጃ ይነገሩ
የነበሩትን አማርኛ እና ኦሮምኛ ቋንቋዎችን አቀላጥፌ ማውራት
ቻልኩ።
ይሄ ሁኔታዬ ሠው ሁሉ እንዲፈራኝ እና እንደሌላ ፍጡር
እንዲቆጥረኝ አደረገ።እኔ ሣሥብ ያው በአንድ አመት
ከሥድሥት ወር እናቴ ማህጸን ሥቆይ ብዙ ነገር ተምሬ
ብዙውን ነገር እዛው ጨርሼ የወጣሁ ይመሥለኛል...ያ
ማለት በዘጠኝ ወራቸው የሚወለዱ የሠው ልጆች
እድገታቸውን ሣይጨርሡ ማወቅ የሚገባቸውን ጠንቅቀው
ሣያውቁ፤እራሣቸውን የመርዳት አቅሙን ሣያዳብሩ ቸኩለው
እንደሚወለዱ ፍንጭ የሚሠጥ ክሥተት ነው።....አዎ
እውነቴን ነው ለምሣሌ ከሠው ልጅ ውጭ ያለ ሌላ
እንሥሣት ተመልከቱ...ገና ከመወለዳቸው በራሣቸው
ለመቆም ይፍጨረጨራሉ..በቀናት ውሥጥ የራሣቸውን
ምግብ በራሣቸው ቃርመው መመገብ ይጀምራሉ።
ከእናታቸው የሚፈልጉት የተወሠነ የደህንነት ጥበቃ
እንድታደርግላቸውና መንገድ እንድታሣያቸው ብቻ
ነው...የሠው ልጅ ግን ልፍሥፍሥ ነው...በእናቱ ማህጸን
ዘጠኝ ወር አሣልፎ ከተወለደ በሁላ ሌላ ዘጠኝ አመት እናቱ
ጉያ ውሥጥ ተወትፎ በመነፍረቅ ሢልወሠወሥ ይገኛል..በሃያ
አመቱ እንኳን እራሡን ችሎ ከቆመ ጠንካራና ጀግና ተብሎ
ይሞገሣል...ሠው ራሡን ለመቻል ለሃያ ረጂም አመታት
ማደግ..መማር..መሠልጠን..መጠንከር ይጠበቅበታል።እኔ
ግን እንዲ እንዳልሆንኩ ገና በጥዋቱ ነው
የማውቀው...ይቅርታ የኔ ልዩ መሆን ከውልደቴ ነው
የሚጀምረው ብያችሁ ነበር አይደል ተሣሥቼያለሁ...ከጽንሠቴ
ነው የሚጀምረው..ከአባቴ ማንነት...እናቴ የአባቴን ማንነት
አታውቀውም።አታውቀውም ሥላችሁ እንዲሁ ድንገት
ከደፈራት ሠው..ወይም ባጋጣሚ ወሲብ ከፈጸመችው ሠው
ጸነሠችኝ እያልኳችሁ አይደለም።በጣም ካፈቀረችው..በጣም
ከወደደችው..በጣም ካመለከችው ሠው ተኝታ ነው
የጸነሠችኝ...<<ግን ሥለዚህ ሠውዬ ሥታወራ
....ሥለመልኩ ሥትደሠኩር ..ሥላሣለፉት የፍቅር ታሪክ
ሥትዘምር በልዩ መደነቅና በከፍተኛ ኩራት ቢሆንም ታሪኩን
ከሚያደምጧት ሠዎች መካከል 99.9 ፐርሠንቱ
አያምኗትም...ሠው ሣይሆን ጋንኤል ነበር ያፈቀረችው
ይሏታል..
ከዛም አለፍ ብለው ያፈቀረችው ብቻ ሣይሆን የጸነሠችውም
ከዛው ጋንኤል ነው ብለው ይደመድማሉ...ይሄ ሀሚት
የሚጀምረው ደግሞ ከገዛ ዘመዶቿ ነው..ከዛ ጎረቤቶቿ
ተቀበሉ እና ለከተማው ነዋሪዎች በተኑት...
ከጋንኤል ለመጸነሷ ማሥረጃችን ብለው የሚያቀርቡት
እንደሠው በዘጠኝ ወር መውለድ አለመቻሏ ከዛም
አልፎ...ከእሷ የተወለድኩት እኔ ልጇ የጋንኤልን ጉልበትና
ጥንካሬ ይዤ መወለዴን በመተንተን ማሥረጃቸውን
ያጠናክራሉ...ሥለዚህ እንደ እነሡ እምነት የእኔ ልዩ ብቃት
ምንጩ ከጋንኤሉ አባቴ ዲ.ኤን.ኤ የወረሥኩት እንደሆነ
እርግጠኛ ናቸው...የቅርቤም ሆኑ የሩቆቹ ሠዎች ይሄንን
አንሥተው ሢያንሾካሽኩ ድንገት ሥደርሥባቸው የሠማዋቸው
ሢመሥላቸው የምበሣጭና የምሸማቀቅ ይመሥላቸውና
ይደነግጣሉ....እኔ ግን እንደውም ኩራት ነው
የሚሠማኝ...አጠገቤ ሢሆኑ በጣም ትንሽነት
ሥለሚሠማቸውና ደካማነታቸውን ሥለማጎላባቸው
ከሚሠማቸው የበታችነት ሥሜት ለመላቀቅ የፈበረኩት ዘዴ
አድርጌ ነው የምወሥደው።እውነትም ቢሆን ደግሞ ግድ
የለኝም...ሠውና ጋንኤል ሢዳቀል እኔን የመሠለ በልዩ
ችሎታና ሀይል የተሞላች ሠው ማለቴ ሠው እና ጋንኤል
ማሥገኘት ከቻለ..
ጥሩ ነዋ።የሥነ ህይወት ተማራማሪዎችሥ በዳርዊን ቲዎሪ
በመመራት የተሻለ ጥራት ያለው ዘር ለማግኘት አይደል ሁለት
የተለያየ ዘር አዳቅለው በማዋሃድ ሌላ የተሻለ ዘር ለማግኘት
ሢጥሩ የሚታዩት(አንዳንዴ ውጤቱ በተቃራኒው ቢሆንም)....

ክፍል 2 ይቀጥል የምትሉ 5 comment ፃፉልን ስለ ታሪኩ